Home ዜና በረሃብ ቸነፈር  ህዝቦቿ ከሚጠቁባቸው ሦስት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ  በግንባር ቀድምትነት እንደምትገኝ አየርላንድ...

በረሃብ ቸነፈር  ህዝቦቿ ከሚጠቁባቸው ሦስት ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ  በግንባር ቀድምትነት እንደምትገኝ አየርላንድ የሰብአዊና ልማት ድርጅቶች የጋራ ጥምረት አስታወቀ፡፡

754

በአፍሪካ ቀንድ ሦስት ሃገራት ውስጥ ለረሃብ ቸነፈር የተጋለጠውን 23 ሚሊዮን ህዝብ ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ የዓለም ማህበረ-ሰብና መንግስታት አፋጣኝ ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የአየርላንድ የሰብአዊና ልማት ድርጅቶች የጋራ ጥምረት ተወካይ አስታወቁ።

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አገሪቱ በብልጽግና ጎዳና ወደፊት  እየረጦች ነች የሚላትን ኢትዮጵያም በረሃብ ቸነፈር  ህዝቦቿ ከሚጠቁባቸው ሦስት ሃገራት መካከል በግንባር ቀድምትነት እንደምትገኝ መግለጫው አመልክቷል።

የአየርላንድ የሰብአዊና ልማት ድርጅቶች የጋራ ጥምረት ተወካይ እና የዶካስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃንአን ሚክናበሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙ ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ሶማሊያ የታየው የረሃብ ቸነፈር ስጋት በአፋጣኝ መግታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የሃገራቱ የረሃብ ቸነፈር ዋና ምንጭ ከሁሉም በላይ የየሃገራቱ የፖለቲካ ውድቀት ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ ከዚህም በተጨማሪ የአየር ለውጥ መዛባት፣ የኮቪድ 19 ቫይረስ መከሰትና እና በየቦታው የሚታዩ ግጭቶችን ቀጠናው ለቀውስ እንደዳረጓት ገልፀዋል፡፡

በሦስቱም ሃገራት ውስጥ በቸነፈር ሰቆቃ ላይ ከሚገኝ 23 ሚሊዮን ህዝብ መካከል 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ያህሉ ህጻናት በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ምክንያት ስቃይ ላይ እንደሚገኙ ያስታወሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ የአይሪሽ የልማት እና የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጥምረት ችግሩን ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸው አረጋግጠዋል፡፡

የየዶካስ  የፖለቲካ መሪዎች በሃገራቱ የተከሰተውን የረሃብ ቸነፈር ችግሮች እንዲፈቱ በአራት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ድርጅቶች በኩል ድርሻቸው እንዲወጡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የእርዳታ ድጋፍ የማሰባሰብና አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና የመሪነት ሚና መጫወት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

የተባባሩት መንግስታት ድርጅት በቀጠናው የተከሰተውን የረሃብ ቸነፈር ለመመከት 4.4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስፈልግ ግምት አስቀምጧል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ ሆኖም እስከአሁን የተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ከታቀደው በእጅጉ ያነሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአለም ማህበረ-ሰብ እና መንግስታት ድጋፍ በማድረግ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት መዘናጋት እያሳዩ ነው ያሉት ኃላፊዋ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት የተሰጡ ግልጽ፣ ተደጋጋሚ እና ተጨባጭ የሆነ የቅድመ ማስጠንቀቂያ የረሃብ አደጋዎችን ችላ በማለታቸው ምክንያት  በሦስቱ ሃገራት ውስጥ የረሃብ ቸነፈሩ ደረጃ በእጥፍ አድጎ 23 ሚሊዮን ህዝብ ማጥቃቱን ገልጸዋል፡፡

አሁን ብቁ የፖለቲካ አመራር እና ተግባራዊ እርምጃ እንፈልጋለን ያሉት ዋና ስራ እስፈጻሚዋ፣ የረሃብ ቸነፈሩ መቀልበስ እምንችለው አሁንም በጥምረት ተግባራዊ እርምጃ  ስንወስድ ነው ብለዋል፡፡

የአየርላንድ መንግስት፣ የሃገሪቱ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች እና የልማት ተቋማት ቸንፈሩን ለመመከት ከዚህ ቀደም ያላቸውን መልካም ተሞክሮዎች በመጠቀም ድጋፍ በማሰባሰብና የዓለም ማህበረ-ሰብን በማነሳሳት ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗዋን አረጋግጠዋል ብለዋል፡፡

አማረ ኢታይ