Home ዜና በሱዳን መጠልያ ካምፕ በከባድ የማህበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ላይ...

በሱዳን መጠልያ ካምፕ በከባድ የማህበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች ላይ እያጋጠማቸው  ያለውን ችግር በአስቸኳይ እንዲፈታላቸው የአሜሪካ የሰኔትና ኮንግረስ አባላት ኣሳስበዋል፡፡

864

የአሜሪካ የልማትና ተራድኦ ድርጅት አገልግሎቱ እንዲያሰፋና በከባድ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ስድተኞች ችግሮቻቸው ለመፍታት እንዲሰራ አባላቱ ውሳኔ አስተላልፈዋል ተብሏል፡፡            

በሱዳን በሦስት የስደተኞች መጠልያ ጣብያዎች የሚገኝ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞች  በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሰብአዊ ተግባሮች እየፈፀመ ያለው ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በሪፖርቱ ያመላክታል፡፡

በዕሙራ ኩቧ፤ ሓምዳይትና ተነድባ ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠው እንደሚገኙ በመግለፅ፣ በቀን ኣንድ ጊዜ ምግብ እንደሚያኙና እንደ ውሃ፣ መጠልያ፣ የትምህርት ቁሳቁሶችና የህክምና አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠባቸው ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ይላል ሪፖርቱ ፣ሰፊ የመጠልያ ስፍራ እጥረት እንዳለና በአንድ ድንኳን ውስጥ ብዙዎች ተጠለው በመኖር  በአከባቢያቸው በሚያገኙት ቁሳቁስ አስተማማኝ ያልሆነ መጠልያ ለመስራት እየተገደዱ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

በዕሙራ ኩቧ ከሚገኝ የስደተኞች መጠልያ መካከልም 23 በመቶ በስተቀር ያሉ መጠልያዎች ጎርፍና ንፋስ በሚከሰትበት ጊዜ እራሳቸው መከላከል የማይችሉበትና አስጊ ሁኔታ ላይ መሆናቸው 22 የአሜሪካ ሴናተሮችና የኮንግረንስ አባላት ወደ የአሜሪካ  የልማትና ተራድኦ ድርጅት /ዩኤስኤ አይዲ/ ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር ደብዳቤ ፅፈዋል፡፡

አባላቱ በፃፉት ደብዳቤ በሱዳን የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በከባድ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ስለሚገኙ  ዩኤስኤ አይዲ በአፋጣኝ እንዲደርስላቸው፣ የተቋረጡ ሰብአዊ እርዳታ እንደቀጥልላችውና ሲሰጣቸው የነበረ አገልግሎት እንዲሰፋ ነው ውሳኔው ያስተላለፉት፡፡

የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋት እየተባባሰ በመምጣቱ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሱዳን እየጎረፉ እንደሚገኙና በዚህ ሳምንት ብቻ ወደ ሶስት ሺ የሚሆኑ ኣዲስ ስድተኞች እንደገቡ ደብዳቤው ኣስታቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 15 የኮንግረስ አባለትና ሰባት ሴናተሮችና ወደ ዩኤስኤ አይዲ በፃፉት ደብዳቤ ድርጅቱ በስደተኞች መጠልያ ጣብያው ያሉ አገልግሎቶችና እንቅስቃሴዎች በተጨባጭ እየሰጠው ያለው አገልግሎትና ያለው ጠቅላላ ሁኔታ ተጨማሪ ማብራርያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡      

የአሜሪካ የልማትና ተራድኦ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር ከሱዳን የስደተኞች ካምፕ ጉቡኝት በኃላ በግንቦት ወር በኣሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክር ቤት ኮሚቴ ቀርበው ከድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ጋር የሚዛመድ ሪፖርት ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡ 

ሄለን ሃፍቱ