Home ዜና በሳውዲ ዓረቢያ የእስር ጊዝያቸውን ያጠናቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው መምጣት ቢፈልጉም...

በሳውዲ ዓረቢያ የእስር ጊዝያቸውን ያጠናቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገራቸው መምጣት ቢፈልጉም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን አልቀበላችሁም በማለቱ መምጣት እንዳልቻሉ BBC ዘገበ፡፡

507

—-

ስደተኞቹ ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላም ባሉበት ቦታ በሚደርስባቸው ስቃይና በደል ምክንያት ለሞትና ለተለያዩ በሽታዎች መዳረጋቸው  በዘገባው አመላክቷል፡፡

በሳውዲ ዓረቢያ በተለያዩ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የእስር ጊዝያቸውን ያጠናቀቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ትውልድ ሃገራቸው መመለስ ባለመቻላቸው አስከፊ ህይወት እየገፉ እንደሚገኙ BBC ስደተኞችን ጠቅሶ ዘግበዋል፡፡

ከ 750 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን መካከል ለደህንነቱ ሲባል ስሙን ንጉስ በማለት ጠርቸዋለሁ ያለው አንድ የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው ኢትዮጵያዊ ለቢቢሲ እንዳለው፣ ከአምስት እስከ 15 ዓመት ተፈርዶብን የእሰር ጊዝያችን ጨርሰናል፤ ወደ ሃገር ቤት ለመመለስ ተመዝግበን ነበር፤ እንዲወስዱን ብንጠይቃቸው ግን መንግስታቹ አንቀበላችሁም ብሏል አሉን ሲል ስለሁኔታ ይናገራል፡፡

ስሙን መግለጽ ያልፈለገና በእስር ውስጥ ያለው አንድ ኢትዮጵያዊ በበኩሉ፣ የእስር ጊዝያችንን በማጠናቀቃችን ከእስር ቤቱ አውጥተው ወደ ሌላ እስር ቤት ለዩን፣፣ ከአሁኑ በኋላ ነጻ ስለሆናቹ ወደ ሃገራቹ ትሄዳላችሁ ብለው ነው የለዩን፤ ሆኖም ግን እስከ ዛሬ ድረስ ማንም ሊደርስልን አልቻለም ሲል ነው ቅሬታውን የገለፀው፡፡

የእስር ቤቱ ዋና አዛዥ መጥቶ አናግሮን ከኢድ በኋላ ወደ ሀገራችን እንደምንሄድ ነግሮን ነበር፤ ነገር ግን አዲስ ነገር የለም ከነበሩበት እስር ቤት ወደ ሌላ የከፋ ቦታ ወስደው  ታጉረናል ብላል፡፡

ውሃ ወደ ሌለበት እና የጦር መሳሪያ ማከማቻ ወደ ነበረ ቦታ ወስደውናል፣፣ መብራት እንኳን የለውም፤ ለምን ብለን ብንጠይቅም የእናንተ ጉዳይ እኛን አይመለከተንም፤ የእስር ጊዝያችሁን ስላጠናቀቃችሁ ጉዳዩን የሚመለከተው መንግስታችሁ ነው በማለት እንደሚገልጽላቸው ዘገባው አመላክቷል፡፡

ከ750 በላይ የሆኑ ስደተኞቹ ያረፉበት ቦታ መሰረታዊ አገልግሎት በማይገኝበት አንድ አደራሽ ውስጥ በመሆኑም ለበሽታና ሞት ተጋላጭ እንዳደረጋቸው በማረዳት በየቀኑ ሰዎች እንደሚሞቱባቸውና ዛሬ ከመካከላቸው ውስጥ ሁለት ሰዎች እንደሞቱባቸው አስረድተዋል፡፡

ስቃዩን የተቃወሙ 17 እስረኞችም ወደ ሌላ ቦታ ወስደው እንዳሰሯዋቸው አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም ከመካከላቸው የአእምሮ ጤና የተቃወሰባቸውና እራቆታቸው የሚሄድ ሰዎች እንደሚገኙባቸው ያስታወሱት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የሳምባ ነቀርሳ እና የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎችም እንዳሉባቸው ለBBC የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ ራሳቸው ያጠፉ ስደተኞች እንዳሉም ነው ያረጋገጡት፡፡

ለፋስሽቱ ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮዽያዊያኑ ላይ ስለ እየደረሰ ያለውን ችግር አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥበት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደረግም አዎንታዊ ምላሽ አለማግኘቱን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷዋል፡፡

አማረ ኢታይ