Home Uncategorized በተመድ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር ለመስራት መወሰኑ ለገለልተኛነት ጥያቄ...

በተመድ የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር ለመስራት መወሰኑ ለገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ተባለ።

549

——-

ዓለም-አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ማህበረ-ሰብ በትግራይ የተፈፀመውን የጀኖሳይድ ወንጀልን ለማጣራት የተቋቋመው  የተመድ አጣሪ ኮሚሽን ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጋር በጋራ እንደሚሰራ ማሳወቁ አስፈላጊ ቢሆንም በምርመራው ሂደት የኮሚሽኑ ነፃነትና አድልዎ የሌለበት የማጣራት ስራ ለመስራቱም ሆነ የግፉ ሰላባዎችንና በህይወት የተረፉትን ወገናችን ማእከል ያደረገ ስራ ለመስራት የገባውን ቃል ችግር ውስጥ ይከተዋል ብሏል፡፡

በዚሁም መሰረት የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና ፋሸስቱ የአብይ ቡድን የሰብአዊ ኮሚሽን የጋራ የምርመራ ግኝትን  እናዳብረዋለን በማለት ያሰተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ አጣሪ ኮሚሽኑ የተሟላና  አድልዎ ሌለበት ምርመራ ስራ  ለማካሄድ እውነታዎችንና ሁኔታዎችን ለመለየት የግፉ ሰለባዎችንና በህይወት የተረፉትን ወገኖች ማእከል ያደረገ የምርመራ ስራን ለማከናወን ከተሰጠው ስልጣን ጋር  የሚቃረን  መሆኑን አመልክቷል፡፡

የጋራ የምርምር ኮሚሽኑ የተጠቀመበት የምርመራ ዘዴና አተገባበሩ አለም-አቀፍ የሰብአዊ መብቶች  ህግ፣ የአለም አቀፍ ጦርነትና ስደተኞች ድንጋጌዎች  ጥሰቶችን የሚያክሉ ወንጀሎችን ለማጣራት የሄደበት መንገድ  ከመስመር የወጣና ፍትህ ያጓደለ መሆኑን የዓለም-አቀፍ የትግራይ  ምሁራንና ባለሙዎች ማህበረ-ሰብ አሳስቧል፡፡

የተመድ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከመጀመሪውኑ ከአንድ ከፋሸስቱ ቡድን ከወገነ ተቋም ጋር በመተባበር ምርመራውን ለማካሄድ መወሰኑ የኮሚሽኑ ተአማኒነትን ሸርሽሮታል ብሏል፡፡

ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ  በሚል ሰበብ በጋራ ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳብ መሰረት የተቋቋመው የፋሽስቱ  ቡድን  የሚኒስቴሮች ግብረሃይልም ቢሆን የፍትህ ስርአቱን ጨምሮ ሁሉም የቡድኑ መዋቅሮች  በትግራይ የጀኖሳይድ ጦርነት በመሳተፋቸው ገለልተኛ ግብረሃይል እንዳልሆነ በማመላከት ይህ  ለአለም-አቀፉ አጣሪ ኮሚሽን መቋቋም ምክንያት እንደሆነም አስረድቷል ፡፡

በመሆኑም  የነዚህ የፋሸስቱ አብይ የጀኖሳይድ ቡድን  አባሪና ተባባሪ አካላት ስራ ውድቅ እንዲሆንና ከነዚህ ተቋማት ጋር ላለመተባበበር እርምጃ እንዲወስድ ለኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ኮሚሽኑ  ሁሉም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የማጣራት ስራ በማካሄድ የግፉ ሰላባዎችንና በህይወት የተረፉ ወገኖችን አመኔታ እንዲያገኝ አሳስቧል ዓለምአቀፍ የትግራይ  ምሁራንና ባለሙዎች ማህበረ-ሰብ፡፡