በትግራይ የተፈጸመውን የጀኖሳይድ ወንጀል እንዲያጣራ በተመድ የተቋቋመው ኮሚሽን ገለልተኛ በመሆን በአስቸኳይ አጣርቶ ወንጀለኞች ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲያቀረብ ተጎጂዎችና የህግ ባለሙያዎች ጥሪ አቀረቡ፡፡
ፋሽስታውያንና ወራሪ ሃይሎች የትግራዋይን ዘር መቀጠል የለበትም እያሉ ሆን ብለው ጥቃት እንዳደረሱባቸው ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሸራሮ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሴቶች ተናገሩ፡፡
የህግ ባለሙያዎች አቶ አዲሱ ብርሃነ እና አቶ ገብረገርግስ ኪዳነ በቡከላቸው በትግራይ የተፈመው ግፍ አለም በሰሙ ባትጠራውም በግልጽ የጆኖሳይድ ወንጀል ተፈጽመዋል ብለዋል፡፡
በትግራይ የተፈጸመው የጀኖሳይድ ወንጀል እንዲያጣራ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ምክር ቤት የተቋቋመው ኮሚሽን ገለልተኛ እና ከወገናዊነት በጸዳ መልኩ ስራውን ማከናወን እንዳለበት የግፉ ሰለባዎች ይናገራሉ፡፡
ኮሚሽኑ በጀኖሳይድ ወንጀሉ የተሳተፉ አካላት በአስቸኳይ አጣርቶ ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲያቀርባቸው የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ሴቶች እና የህግ ባለሙያዎቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የጀኖሳይድ ወንጀል ለማጣራት ወደ አዲስ አበባ የገባው የተመድ አጣሪ ኮሚሽን የፋሽስቱ አብይ ቡድን ተባባሪ የሆነው የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያጠናውን ሪፖርት እናዳብረዋለን ማለታቸውን በትግራይ መንግስት በኩል ተቀባይነት እንደማይኖረው መገለጹ ይታወቃል፡፡
ወ/ሚካኤል ገ/መድህን