Home ዜና በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው ጄኖሳይድ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥበት ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ  ሰላማዊ...

በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው ጄኖሳይድ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥበት ዲያስፖራ ማህበረ-ሰብ  ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ጠየቁ፡፡

764

——

የፋሽስቱ አብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ባለው ጄኖሳይድ ከስድስት መቶ ቀናት በላይ በማስቆጠሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትኩረት ሰጥቶ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥበት በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ የትግራይ ያስፖራ ማህበረ-ሰብ  ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ጠየቁ፡፡

እየተካሄደ ያለው የጄኖሳይድ ጦርነት ሰልፈኞቹ የአለማቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል ብለዋል፡፡

በዋሽንግተን፣ በመሪላንድ እና በቨርጂኒያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች  በዋሽንግተን ዲሲ  በመሰባሰብ የፋሽስቱ ቡዱን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው የጄኖሳይድ ጦርነት በመቃወም ሰለማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ 

በሰላማዊ ሰልፉም የፋሽስቱ ቡዱን ለትግራይ ህዝብ የእርዳታ እህል እንዳይደርስ ወደ ትግራይ የእርዳታ እህል ያጫኑ መኪኖች በተፈለገው መጠን እንዳይገቡ በፈጠረው ክልከላ ተከትሎ የተከሰተው ሰው ሰራሽ ረሀብ ሊቆም ይገባዋል ብለዋል፡፡

አሜሪካና ሌሎች የአለም አቀፍ ተቋማት የትግራይ ጆኖሳይድ እንዲያበቃ በፋሽስቱ የአብይ አህመድ ቡድን ተፅኖ ማሳደር እነዲያሳድሩ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል፡፡

ሰልፈኞቹ በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው የጄኖሳይድ ወንጀል  በሌላ አለም ታይቶ እንደማይታወቅ በመግለፅ ከ 600 መቶ ቀናት በላይ ያስቆጠረውን ከበባ እና ክልከላ እንዲያበቃም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  ለጉዳዩ ትክረት ሊሰጥ ይገባዋል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ እነዚህ የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረሰብ 34ኛው የሰማእታት ቀን አክብረዋል ፡፡

መአዲ ሃይለ