Home ዜና በትግራይ በርሃብ ምክንያት ከ200 000 በላይ ህፃናት እንደሞቱ  ተገለፀ፡፡

በትግራይ በርሃብ ምክንያት ከ200 000 በላይ ህፃናት እንደሞቱ  ተገለፀ፡፡

836

በትግራይ በርሃብ ምክንያት ከ ሁለት መቶ ሺ በላይ ህፃናት እንደሞቱ መቀመጫዉን ኒዉዘርላንድ አምስተርዳም  ያደረገዉ  Trouw የተባላ የመረጃ ማእከል ገልጿል፡፡

የመረጃ ማእከሉ በዉቕሮ ከተማ የሚገኙ አባ ኦላራን የተባሉ የሃይማኖት መሪ ዋቢ በማድረግ እንደዘገበዉ የትግራይ ህዝብ ሰቆቃ በአለም ማህበረ-ሰብ ዘንድ ተረስቷል ሲል ገልፆታል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ ያወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት በከበባና ክልከላ ተጠናክሮ እንደቀጠለና የትግራይ ህዝብ በከባድ ችግር ዉስጥ እንደሚገኝ የሚያትተው  Trouw መረጃ ማእከል ዘገባ  የዚህ ዉጤትም ከ አንድ እስከ አምስት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ  ከሁለት መቶ ሺ በላይ ህፃናት በርሃብ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ብሏል ፡፡

Trouw ይፋ  ያደረገዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ በርሃብ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው  ሁለት መቶ ሺ ህፃናት ባለፉት ስድስት ወራት ዉስጥ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ 

መቀመጫዉን  አምስተርዳም ያደረገዉ  Trouw የተባላ የመረጃ ማእከል በርሃብ ምክንያት የሞቱት ህፃናትና በከባድ ችግር ዉስጥ የሚገኙት ህፃናት ጉዳይ የአለም ማህበረሰብ መፍትሄ ማጣቱ  በጣም አሳዛኝ ነዉ ሲል ገልፆታል፡፡

ስለ ህፃናት መብት የሚሟገተው በተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት UNCEF  ባለፈዉ ዓመት በትግራይ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ህፃናት መሞታቸውን የሚገልፅ ሪፖርት ማውጣቱ የሚታወስ ነዉ፡፡

ፍረወይኒ መንገሻ