የአገው ህዝብ ራሱ በራሱ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብቱ ተነፍጎ የራሱ ክልል ሳይኖረው በአማራ ክልል ስር ሆኖ የአማራዊነት ካባ ለብሶ እንዲጓዝ ተደርጎ የህዝቡ ችግሮች ለመፍታት ይልቅ የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች አጀንዳዎች በመጠመዳቸው ለከፋ ችግር አጋልጠውት ይገኛሉ።
የፋሽሽቱ ዓብዪ አህመድ ቡድን እና ተስፋፊው የአማራ ሃይሎች የተለያዩ መሰረተ ልማቶች መዘርጋትና ማስፋፋት ካለመቻላአውና ላጋጠሙ ችግሮች ከመፍታት በላይ በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈቱት የጀኖሳይድ ጦርነት ለአገው ህዝብም ተርፎ፣ ተጀምረው የነበሩትን የልማት ተቋማት በአምባገነኑ የኢሳያስስ አፈወርቂ ቅጥረኛ ሰራዊት ካወደማቸው አንዱ የብርቢጣ ንኡስ ወረዳ የሴርያ ጤና ጣብያ ነው።
በዚህም ጤና ጣብያው በመውደሙና በመዘረፉ ምክንያት የአከባቢው ነዋሪዎች ለከፋ በሽታና ሞት እየተጋለጡ እንደሚገኙ በህክምናው አገልግሎት አጥተው ሲጠባበቁ ያገኘናቸው ወገኖች ገልጸዋል።
በሴርያ ጤና ጣብያ የጤና ባለሙያ አቶ ጸጋይ ደግፍ ፣ ጤና ጣብያው ለአጎራባችኝም ጭምር አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸው በዚህ ሰዓት የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንደተቸገረ እና የመዋለጃ እና አጠቃላይ ንብረቱ በአምባገነኑ የኢሳያስ ቅጥረኛ ሰራዊት በመዘረፉና በመውደሙ የህክምና አገልግሎቱ መስተጓጎሉ አስረድቷል።
የንኡስ ወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አለፈ ብርሃኑ በበኩላቸው የሴርያ ጤና ጣብያ የአምባገነኑ የኢሳያስ ታጣቂዎች የጦር ካምፕ አድርጎት የቆየ መሆኑና አስታውሰው የአለም አቀፍ መንግስታትም ሆነ የዲያስፖራው ማሕበረ ሰብ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይና መከራ ተገንዝቦ ከተጎዳው የአገው ሕዝብ ጎን ቆሞ መፍትሄ እንዲሰጧቸውና ለተጎዳው ሕዝብ ድምጽ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።
የፋሽሽቱ ዓብዪ አህመድ ቡድን እና ተስፋፊው የአማራ ኢሊቶች የህዝብ ቅቡልነታቸው በመውረዱ ጭንቅ የወለደው ያለፉት የአገው የንግስነት ዘመናት ታሪክና ቅርስ አውሮሶ ያለፈው መንግስትነቱ የጨለማ ዘመን እንዳሉት ሁሉ አሁንም አገውን አምበርክኮ ለመግዛት መንግስታዊ ስላቅ መስጠት ቀጥለውበታል።