በአፍሪካ ህብረት አዘጋጅነት በትግራይ መንግስትና በፋሽስቱ የአብይ ቡድን መካከል በመጪው እሁድ መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም ሊካሄድ ታስቦ የነበረው የሰላም ድርድር መራዘሙን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘገበ።
ሮይተርስ የዜና ወኪል የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የታቀደው የሰላም ንግግር እንዲዘገይ የተደረገው በሎጀስቲክ ምክንያት ነው።
በተመሳሳይ የቀድሞ የኬንያው ፕሬዝዳንት እሁሩ ኬንያታ በሰላም ውይይቱ ለመገኘት እንደማይችሉ ዛሬ ያስታወቁ ሲሆን በቀጣይ ስለውይይቱ ሂደት ግልፅ የሆነ ማብራርያ እንደሚሹም ገልፀዋል።