ከአምባሳደር ማይክ ሃመር በተጨማሪም በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳዳር ትሬሲ አን ጃኮብሰንም የሚገኙበት ይህ ልኡክ ቡዱን በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርስ በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎለታል።


ልኡኩ ከትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ ከአፍሪካ ህብረት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ እንዲሁም ከሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። በ ታሪክ ፍስሃ