በኢትዮጵያ አጋጥሞ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስና የብድር እዳ መቆለል፣ አበዳሪ አገራት የሚሰጡት ብድር ለወታደራዊ አገልግሎት እንዲውል በመደረጉ መሆኑን አበዳሪ አገራትና የአለም ባንክ ገልፀዋል፡፡
አገሪቷ ባለፉት ሁለት አመታት ወደ ጦርነት መግባትዋን ተከትሎ ከአገር ውስጥና ከውጭ አገራት የተበደረችው ከ56 ቢልዮን በላይ ዶላር መድረሱን የአለም ባንክ አስታወቀ፡፡
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ አጋጥሞ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስና የብድር እዳ መቆለል በዋነኛነት ወደ ጦርነት በመግባትዋ መሆኑን አበዳሪ አገራት ገልፀዋል፡፡
የፋሪስ ክለብ ተወካይ ሚስተር ዊልያም ሩች ከቡዱን 20 ስብሰባው አስቀድሞ ለፋሽስቱ ቡዱን ተወካይ ለሆነው እንደገለፁለት ፈረንሳይና ቻይና የአገሪቱን እዳ እንዲቃለል ፍላጎት እንኳ ያላቸው ቢሆን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው ጦርነት እንዲያቆምና የስልክ፣ የባንክ አገልጎሎቶች ጨምሮ ሌሎች የተዘጉ አገልግሎቶች በቅድሚያ ሊከፈቱ ይገባል ማለታቸው የአለም ባንክ ሰነድ ዘግቧል፡፡
እንዲሁም ያልተገደበ ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ ማድረግና በትግራይ ህዝብ ላይ ኢሰብአዊ እልቂት እንዲፈፀም ያደረጉት ወደ ህግ እንዲቀርቡ ማድረግ የአገሪቱ መንግስት ተቀዳሚ ተግባራት ሊሆን ይገባል ብሏል የአለም ባንክ ሰነድ፤
በኢትዮጵያ ባለው ክምር እዳ ዙሪያ ለመወያየት በፈርንሳይና በቻይና አነሳሽነት ሶስት ጊዜ ለውይይት ቢቀመጡም በቅድሚያ የፋሽስቱ ቡዱን ሊፈፅማቸው የተነገሩት መቅደም አለባቸው ብለዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ከአቅም በላይ ያለው ክምር እዳ ካልተፈታ አገሪቷን ወደ ከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ ልትገባ እንደምትችል የአለም ባንክ ያዘጋጀው ሰነድ አስረድቷል፡፡
በአገሪቱ ያለው የእዳ መብዛት፣ ያልተረጋጋ ገበያና ከፍተኛ የዋጋ ንረት ተጠናክሮ መቀጠሉ ሌላው ስጋት ነው ተብሏል፡፡
በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሪ ሚዛን ከአገሪቷ አጠቃላይ አመታዊ ገቢ ጋር ሲነፃፀር ከሁለት ነጥብ ስምንት ወደ አራት ነጥብ አንድ መውረዱ የአንድ አገር ያልተረጋጋ ኢኮኖሚ ማሳያ ነው ብሎታል የአለም ባክን ሰነድ፤
ለዚህ ዋነኛ ምንክያት በአንድ አመት ብቻ ከአገሪቱ አጠቃላይ ገቢ ከዜሮ ነጥብ ስምንት በመቶ በላይ ለወታደራዊ አገልግሎት እንዲውል በመደረጉ የአለም ባንክ አስረድቷል፡፡
በ2014 የበጀት አመት መጀመሪያ የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ በ30 በመቶ መቀነሱን ተከትሎ አበዳሪ አገራት የሚሰጡት ብድር ለጦርነት እያዋለው በመሆኑ ትኩረት ሊያደርጉለት እንደሚገባ የአለም ባንክ ማሳሰቡን ሰነዱን አመልክቷል፡፡
በፋሽስቱ የአብይ ቡድን የምትመራው አገር የእዳ መስተካከያ እንዳይደረግላት በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ካለው የጀኖሳይድ ጦርነት በተጨማሪ በተለያዩ የአገሪቱ አካባበዊች ጦርነትና ግጭቶች መበራከታቸው እንዲሁም የአማራ ተስፋፊዎችና የአምባገነኑ ኢሳያስ የሰላም ድርድሩ እንዳይካሄድ አገሪቷን እንዳትረጋጋ ከማድረጉም በተጨማሪ ለኢኮኖሚው መላሸክ የጎላ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብሏል የአለም ባንክ ሰነድ፡፡
BBCና ኳርቲዝ አፍሪካ ድረገፅ የአለም ባንክና የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ጠቅሰው እንደዘገቡት የደርግ ስርዓት በወደቀበት ወቅት የአሪቷ የውጭ ብድር ዘጠኝ ቢልዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ከአስር አመታት በኃላ እዳው ወደ ሁለት ነጥብ ሁለት ቢልዮን ዶላር መውረዱን አውስተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአገር ውስጥና ከውጭ አገራት የአገሪቱ መንግስት የወሰደው ብድር ጨምሮ የአገሪቱ እዳ ከ30 ነጥብ 36 ቢልዮን ዶላርወደ 56 ነጥብ 56 ቢልዮን ዳላር መድረሱን አመላክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ እዳ ከአመታዊ የአገሪቷ ምርት ጋር ሲነፃፀር ግማሽ ያህል መድረሱን፣ የምጣኔ ሃብት ባለመያዎች እንደገለፁት ደግሞ የፋሽስቱ ቡዱን ብድሩ ተጠቅሞ የአገሪቷን ገቢ በሚያጎለብቱ ስራዎች እንዲውል ባለመደረጉ ፣ እንዲሁም አዳዲስ የስራ መስኮች በሚያስገኙ ስራዎች እነዲውል ባለመደረጉና የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ላይ እንዲውል አለመደረጉ እዳው እንዲቆለል አድርጎታል ብለዋል፡፡
ተካ ጉግሳ