Ethiopian insight ድረ-ገጽ እንደዘገበው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ጦርነቱ ስልጣኑን ለማቆየት እንደ አንድ ስልት እየተጠቀመበት ነው፡፡ Ethiopian insight ድረ-ገጽ በዘገባው፣ በኦሮሚያ እና በተስፋፊው የአማራ ታጣቂዎች መካከል በኦሮሚያ ምዕራብ አከባቢ እየተዋጉ ያሉት ሃይሎች በአከባቢው ሰፍረው የነበሩ የፋሽስቱ የአብይ ቡድን የጸጥታ ሃይሎች ወዲያውኑ ከቦታው እንደለቀቁ ወዲያውኑ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ነው፡፡
በሰላማዊያን ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል፤ በሚል ሰበብ በሁለቱም ታጣቂዎች መካከል ለተቀጣጠለው ጦርነት ኃላፊነቱ ማን ይውሰድ በሚለው ጥያቄ ላይ አንዱ ሌላውን ይከሳል፡፡
የተስፋፊው የአማራ ሃይል የማህበረ-ሰብ አንቂዎች ነን ባዮች በኦሮሞ ነጻነት ጦር ላይ የተከፈተው ጦርነት በአማራ ሰላማዊያን ሰዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃትን ለመከላከል ነው ሲሉ የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት የሚደግፉ ሃይሎች በበኩላቸው ተስፋፊዎቹን የአማራ ታጣቂዎችን ተጠያቂ እያደረጉ ነው፡፡
አንዳንድ የአማራ ክልል ተፎካካሪ ነን ባይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለግጭቱ መከሰትና መባባስ የፋሽስቱ ቡድን እና የኦሮሚያ የፋሸስቱ የአብይ ቡድን ግብረአበሮችእጃቸው አለበት በማለት ይወነጅላሉ፡፡
የኦሮሚያ ብሄርተኛ ቡድኖች በበኩላቸው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች እየተዋጉ ያሉት የኦሮሞ ህዝብን ከሚደርስበት ጭቆና ነጻ ለማውጣት እንጂ የአማራ አንቂዎችና የፖለቲካ ሃይሎች እነደሚሉት የአማራ ሰላማዊያን ሰዎችን ለማጥቃት አይደለም ሲሉ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በሰላማዊያን ሰዎች ላይ ጥቃት ይፈጽማል የሚለውን ውንጀላ አንደማይቀበሉት እየገለጹ ሲሆን በምዕራብ ኦሮሚያ በአማራ ሰላማዊያን ሰዎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና በደል ተጠያቂው የፋሽስቱ ቡድን ብቻ ነው ብለዋል፡፡
በምዕራብ ኦሮሚያ በተደጋጋሚ እየተካሄደ ነው የሚባለው ጦርነት የታሪክ ድግግሞሽ የሚታይበትና የኃሊዮሽ የተስፋፊዎቹ የአማራ ብሄርተኛ ሃይሎች የተዛባ የፖለቲካ እና የታሪክ ትርክት ቁርሾ ወጤት ነው በማለት የኦሮሞ ብሄርተኛ ሃይሎች እየገለጹ እንደሚገኙም ነው ድረ ገጹ ያስታወቀው፡፡
በአከባቢው በአማራ እና በኦሮሚያ ማህበረሰቦች መካከል ግጭቶችን የተጀመረ እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር ከ1990ዎቹ ጀምሮ ነው ብሏል Ethiopian insight ድረ-ገጽ፡፡ የአማራ ብሄርተኛ ተወላጆች የኦሮሞ ማህበረ-ሰብ በአከባቢው ሰፍረው በነበሩ የአማራ ማህበረ-ሰብ አባላት ላይ ግጭት መቀስቀሳቸውን ተከትሎ ነው ሲሉ፣ የኦሮሞ ብሄርተኛ ሃይሎች በበኩላቸው ሁኔታው ወደ 19ኛው ክፍለ ዘመን የኋላ ታሪክ የሚመልሰን የታሪክ ክስተት ነው ማለታቸውን ድረ ገጹ አስታውቋል፡፡
ያም ሆነ ይህ በሁለቱም ማህበረ-ሰብ አባላት ምዕራብ ኦሮሚያን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች የተከሰተውና የተቀጣጠለው ጦርነት በሺህ የሚቆጠሩ የሁለቱም ብሄረሰብ ተወላጅ ሰለማዊያን ሰዎችን ህይወት እያጠፋ በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያፈናቀለና አያሌ ንብረቶችን እያወደመ መቀጠሉን ነው ዘገባው ያስታወቀው፡፡
በአማረ ኢታይ