Home ዜና በጀግናው የትግራይ ሰራዊት በጦር ግንባር የተማረኩ ከ4200  በላይ የፋሽስቱ አብይ ቡድን የጦር...

በጀግናው የትግራይ ሰራዊት በጦር ግንባር የተማረኩ ከ4200  በላይ የፋሽስቱ አብይ ቡድን የጦር ምርኮኞች በምህረት ወደ ቀያቸው ተሸኙ።

2616

አለም አቀፍ የጦር ምርኮኛ አያያዝ ህግጋትን በመጠበቅ ከዘጠኝ ወራት በላይ በትግራይ ሰራዊት የምርኮኞች ማእከል የከረሙት የፋሽሽቱ የጦር ምርኮኞች ዳግም ምህረት የተደረጎላቸው ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል፡፡

በእርግጥ  ይህ የትግራይ መንግስት ተግባር ከአለም አቀፍ  ህግና ድንጋጌ በላይ የትግራይ ህዝብ  ሰብአዊነት ምህረት አድራጊነት የስነ ልቦና ልእልና እና ጀግንነት ለዘመናት  በትግራይ ህዝብ ተጠብቀው ከቆዩት መልካም እሴቶች የተቀዳ ስለመሆኑ አያጠራጥርም:: የተሸኙት የጦር ምርኮኞችም በአንደበታቸው ይህንን አረጋጠዋል:: 

ምንም እንኳ በየኣቅጣጫው ዘምተው በትግራይ ህዝብ ላይ አያሌ ጭፍጨፋ እና ግፍ ቢፈፅሙም  በጦር ሜዳ ግምባር ጠላቶቹን መማረክ ብቻ ሳይሆን በሰብአዊነት ምርኮኞቹን ተንከባክቦ የማቆየት የረጅም ጊዜ ታሪክ ከቀደምት ኣባቶቹ የወረሰው ጀግናው የትግራይ ሰራዊት ህዝብና መንግስት  ለምርኮኞቹ ምህረት በማድረግ ወደ ቤተሰቦቻቸው በሰላም ሸኝቷቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ህዝብ የምርኮኞቹን ረሀብ እና ጥም  ከመጋራት  ባሻገር  ቁስላቸውን  ፈውሷል፤  29 ነፍሰጡር ሴት ምርኮኞችንም  በሰላም በማዋለድ  ልጆቻቸውን  እንዲያቅፉ ኣድረጓቸዋል::

የሶማሌ ተወላጅ እና በምርኮኞች ማእከሉ የጤና ባለሙያ የሆኑት ዮሱፍ ኢብራሂም  ነብሰ-ጡሮች ሆነው ተማርክው ልጆቻቸው ይዘው  በምህረት ከተሸኙት በተጨማሪ ከ4200 በላይ ሙርከኞች መሸኘታቸው  የትግራይ ህዝብ ይቅር ባይነት የሚያረጋግጥ ሀቅ ነው ብልዋል፡፡

ሄለን ወ/ዮሃንስ