Home ዜና ብቸኛ የዜማ  ፈላስፋው የቅዱስ ያሬድ ልደትን የሚዘክር ልሳነ ግዕዝ ቅዱስ ያሬድ የጉባኤ...

ብቸኛ የዜማ  ፈላስፋው የቅዱስ ያሬድ ልደትን የሚዘክር ልሳነ ግዕዝ ቅዱስ ያሬድ የጉባኤ መድረክ በአክሱም ከተማ ተካሂዷል፡፡

1382

የቅዱስ ያሬድ ወርቃማ ስራዎችን በመሰነድ ለአለም ከማስተዋወቅ ባሻገር የጥናትና ምርምር ማዕከል እንዲሆን የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

#አክሱም ዩኒቨርስቲ፡ አክሱም ፅዮን ርዕሳነ አድባራት ወገዳማት እና የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት በጋራ ባስተባበሩት ልሳነ ግዕዝ ቅዱስ ያሬድ የጉባኤ መድረክ በአክሱም ከተማ ታስቦ ዉሏል፡፡

በጉባኤዉም የተለያዩ የአብያተ-ክርስትያናት ሊቃዉንት ፡ የዩኒቨርስቲ መምህራን እንዲሁም የተለያዩ የማህበረ-ሰብ ክፍሎች የተገኙ ሲሆን የዜማ  ፈላስፋው ሊቀ-ሊቃዉንት ቅዱስ ያሬድ ለዘመናዊና መንፈሳዊ ትምህርት ያበረከተዉ የእዉቀት ፀጋ ተዳሷል፡፡

“ቅዱስ ያሬድ ለሰዉ ልጅ ባህል ያበረከተዉ አስተዋፅኦ” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፋቸዉን ያቀረቡት የዘርፉ ምሁራን ብቸኛ የዜማ  ፈላስፋ የሆነዉ ቅዱስ ያሬድ በዘመኑ የነበረው የስነ-ሀሳብና የትግራይ ህዝብ የታሪክ እርከን በጥናትና ምርምር ታግዞ ለትዉልድ መተላለፍ ይገባዋል ብለዋል፡፡

“የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች በዘመናቸዉ ታሪኩን ለመንጠቅ ዕረፍት ኣግኝተዉ አያዉቁም” ያሉት ምሁራኑ የቅዱስ ያሬድ ወርቃማ ስራዎችን በመሰነድና በመቅረፅ ለአለም ከማስተዋወቅ ባሻገር የጥናትና ምርምር ማዕከል እንዲሆን የተቀናጀ ስራ መስራት ከሚመለከታቸዉ አካላት የሚጠበቅ ትልቅ የቤት ስራ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ በአክሱም ዩኒቨርስቲ የምርምርና የማህበረ-ሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር መርሃዊ አብርሃ የቅዱስ ያሬድ ስራዎችን ስናወሳ ጠላቶች የማንነታችንን እና ክብራችንን መገለጫ የሆነዉን ቅርሳችንን በመዝረፍ ፡በመቀማትና በማዉደም ከአለም ታሪክ ለመፋቅ ትልቅ ጥረት አድርገዋል ብለዋል፡፡

የዜማዉ ፈላስፋ ቅዱስ ያሬድ ከወላጅ አባቱ ይስሃቅና ከወላጅ እናቱ ታዉሊያን በ503 ዓ.ም በአክሱም ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ መደባይ በሚባል ቦታ መወለዱን የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፣ ቅዱስ ያሬድ ግዕዝ፣ እዝል፣ አራራይ የሚባሉ የዜማ ቅኔዎች ለዓለም ህዝብ ያበረከተ ሊቅ መሆኑን ይታወቃል፡፡

ሙሉብርሃን ዳርጌ