Home ዜና አለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ምሁራን የአቋም መግለጫ

አለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ምሁራን የአቋም መግለጫ

1094

በትግራይ እየታየ ያለው ሰብአዊ ቀውስ ወደ ከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት የአብይ ቡዱን ሰብአዊ እርዳታን ወደ ትግራይ ከማስገባት ጀምሮ ሌሎች ማህበራዊ አገግሎቶት እንዲከፍት የአለም ማህበረ-ሰብ ተፅእኖ ሊያሳርፍ እንደሚገባ አለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ሙሁራን ማህበረ-ሰብ ጠየቁ፡፡
በትግራይ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን ክልከላና ከበባ እንዲያበቃ ፈጣን እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ የባለሙያዎችና የሙሁራን ማህበረ-ሰቡ ባወጡት የአቋም መግለጫ ጠይቀዋል፡፡
የባለሙያዎችና የሙሁራን ማህበረሰቡ ባወጡት ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ ከሳምንት በላይ ያስቆጠረው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማሳለጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ የገቡትን ቃል በመጣስ የአብይ አሕመድ ባለስልጣናት ለቃላቸው ታማኞች ሊሆኑ አልቻሉም ብሏቸዋል፡፡
በትግራይ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ከቁጥጥር ውጭ ከመሆኑ በፊት የአብይ መንግስት ወደ ትግራይ ሰብአዊ እርዳታው በሁሉም የመግቢያ በሮች ያለገደብ ከማቅረብ ጀምሮ ተገቢውን ቁጥጥር፣ ክትትልና ሪፖርት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል፡፡
የአብይ ቡዱን ሰብአዊ እርዳታውን ለማስገባት ፈቃደኝነቱን ከገለፀ በኃላ የትግራይ ሰራዊት ከያዛቸው የዓፋርና የአማራ በቅድሚያ መልቀቅ አለበት የሚለው ቅድመ ሆኔታ ማስቀመጡ የሰብአዊ እርዳታ ለማቅረብ ሲባል በጊዜያዊነት ግጭትን የማቆም ስምምነት /cessation of hostilities/ የሚጣረስ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን ማህበረሰቡ ባወጣው የአቋም መግለጫ አስረድቷል፡፡
ከ17 ወራት በላይ ባስቆጠረውና በትግራይ ህዝብ ላይ እየተካሄደ ባለው የጆነሳይድ ጦርነት የኢትዮጵያና የአምባገነኑ ኢሳያስ ወታደሮች እንዲሁም የአማራ ተስፋፊ ልዩ ሃይልና የሚሊሻ አባላት በህዝቡ ላይ በቀላሉ ሊረሱ የማይችሉ ግፎች መፈፀማቸው የአቋም መግለጫው አመልክቷል፡፡
እነዚህ የሰራዊት አባላት በእቅድ የጅምላ ግድያ ከማካሄዳቸው በተጨማሪ መጠነ ሰፊ ፆታዊ ጥቃትና አስገድዶ የመድፈር ተግባራት በትግራይ እናቶችና ህፃናት ላይ መፈፀማቸው የማይረሳ ክስተት መሆኑን የአቋም መግለጫው አስረድቷል፡፡
የአብይ ቡዱን ቀደም ሲል በትግራይ ህዝብ የፈፀማቸው ጥቃቶች ሳይበቁት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመበት መሆኑን የገለፀው ማህበሩ ይህም በትግራይ ህዝብ የተፈፀመ ጆነሳይድ መሆኑን አውቆ የአለም ማህበረ-ሰብ ጉዳዩን በአንክሮ ሊከታተለው ይገባል ብለዋል፡፡
በቅርቡ በጌንት ዩኒቨርስቲ በተካሄደው ጥናት 500 ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ጦርነቱ ባስከተለው ቀውስ፣ በግድያ፣ በመድሃኒት እጥረትና በረሃብ መሞታቸው ማረጋገጡም የጠቀሰው የማህበሩ የአቋም መግለጫ የዚሁ ሰላባ ከሆኑት መካከልም የዩንቨርስቲ ሙሁራንና የጤና ባለሙያዎች ይገኙባቸዋል ብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃትና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የአብይ ቡዱን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ክልከላን ከማንሳት በተጨማሪ የነዳጅ፣ የመድሃኒት፣የባንክ የኤሌክትሪክና የስልክ አገልግሎቶች ጭምር ሊከፈቱ ይገባል ብሏል የኣቋም መግለጫው፡፡
የአለም ማህበረ-ሰብ በዋነኛነት ደግሞ የተባበሩት መንግስታት፣ የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ በማንኛውም አማራጭ እንዲገባ መፍቀድና መከታተል ይኖርባቸዋል ብሏል፡፡
በዋነኛነት ደግሞ ሰብአዊ እርዳታን አስመልክቶ የአብይ ቡዱን የሚደርጋቸው እንቅስቃሴዎችና እየወሰዳቸው ያሉት አቋሞች የአለም ማህበረ-ሰብ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል ብሏል የአለም አቀፍ የተጋሩ ባለሙያዎችና ሙሁራን ማህበረ-fሰብ የአቋም መግለጫ፡፡
ተካ ጉግሳ