Home ዜና ኢትዮጵያ የግጭቾች መነሃሪያ መሆንዋን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ  UN, OCHA ባወጣው ሪፖርት...

ኢትዮጵያ የግጭቾች መነሃሪያ መሆንዋን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ  UN, OCHA ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርገ፡፡

868

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ኢትዮጵያ የግጭቾች መነሃሪያ መሆንዋን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ እርዳታ ጽህፈት ቤት UN, OCHA ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርገ፡፡

በአንድ ሳምንት ብቻ  ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሊቀጠፍ መቻሉንም  OCHA በድረ-ገጽ አስፍሯል፡፡

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ በጦርነት እየታመሰች የምትገኘው ኢትዮጵያ አሁንም መረጋጋት ተስኗት የንጹሃን ዜጎች ህይወት እንደ ቅጠል  የሚረግፍባት አገር ሆናለች፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት UN, OCHA ባወጣው ሪፖርትም በኢትዮጵያ በአንድ ሳምንት ብቻ ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሊቀጠፍ መቻሉን ይፋ አድርጓል፡፡

ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ ሶስት 2014 ዓም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ እና በደቡብ ብሔር ብሔረ-ሰቦች በተከሰቱ ዘጠኝ የቡድን ግጭቶች ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በርካታችን ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል ብሏል ሪፖርቱ፡፡

ህይወታቸው ካለፉት መካከልም ከ20 በላይ ንጹሃን ዜጎች መሆናቸውን OCHA አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የግጭቶች መናሀሪያ እንድትሆን ያደረጋት ደግሞ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አጠፋለሁ በማለት በከፈተውና በከሸፈው ዘመቻ እና አክራሪው የፋኖ ቡድን በንጹሃን ዜጎች በወሰዱት የቂም በቀል እርምጃ ነው ብሏል፡፡

በዚህም  በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትና በፋሽስቱ ቡድኑ ቅጥረኛ ወታደሮች መካከል በጉጂ ዞን አምስት ግጭቶች የተከሰቱ ሲሆን በዚህም የበርካታ ሰላማውያን ሰዎች ህይወት ማለፉን ተገልጿል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ምት መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ቅጥረኛ ሰራዊት በንጹሃን ዜጎች ላይ በወሰደው  የበቀል እርምጃ በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውን ነው ኦቻ ያስታወቀው፡፡

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አክራሪው የፋኖ ቡድን ንጹሃን የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጉዳት ማድረሱንም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ 

በዚሁ ዞን ፋኖ ንጹሃን ኦሮሞዎችን ከመግደሉ በተጨማሪ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ጦርነት ከፍቶ በቦታው በማቆያ ካምፕ ተጠልለው የነበሩት ተፈናቃዮች ላይ ጉዳት መድረሰንም ተገልጿል፡፡

በቦታው ከብት ይጠብቁ የነበሩት ሁለት የኦሮሞ ተወላጅ ህጻናትም በፋኖ ቡድን አስቃቂ በሆነ መልኩ መገደላቸውም ነው ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡ 

በአማራ ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳም ንጹሃን የአፋር ተወላጆች መገደላቸውን ተከትሎ በአፋርና በአማራ ሀይሎች መካከል በተነሳው ግጭት የበርካታ ሰላማውያን ሰዎች ህይወት ማለፉን በሪፖርቱ ተጠቅስዋል፡፡

በደቡብ ብሔር ብሔረሶቦች እና ህዝቦች ክልል ዘጠኝ የኦሮሞ ተወላጅ በማንነታቸው ምክንያት እንደተገደሉ የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ በዚህም በበርካታ የክልሉ አካባቢዎች ግጭቱ ተባብሶ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል ብሏል ኦቻ ባወጣው ሪፖርት፡፡

በጋምቤላ ክልልም በጋምቤላ ነጻነት ሰራዊት እና በክልሉ ሀይሎች መካከል በተከፈተው ጦርነት በርካቶቸን ለጉዳት መዳረጉን ነው የተገለጸው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዩኤን ኦቻ ይዞት በወጣው ሪፖርት ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ባለፉት አራት አመታት በኢትዮጵያ ከሶስት ሺህ በላይ ግጭቶች መከሰታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

ይብራህ እምባየ