Home ዜና ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ፋሽስቱ አብይ  እንዳይሳተፍ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች...

ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ፋሽስቱ አብይ  እንዳይሳተፍ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የህግ መወሰኛ ም/ቤት   ስምምነት ላይ  ደረሱ፡፡

1102

የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን በሚቀጥለው ታህሳስ ወር ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ፋሽስቱ አብይ  እንዳይሳተፍ ቁልፍ የሚባሉ የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ታወቀ፡፡

ፋሽስት አብይ አሕመድ በስብሰባው ላይ እንዳይሳተፍ ስምምነት ላይ የደረሱት ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጀው የጀኖሳይድ ጦርነት ፆታዊና ወሲባዊ ጥቃትን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀሙ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ፋሽስቱ ፆታዊ ጥቃትን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም በ10 ሺዎች በሚቆጠሩ የትግራይ ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ አስገዳጅ ወሲባዊ ጥቃት መፈፀሙን የሰኔት አባላቱ በማረጋገጣቸው ባይደን በመጪው ታህሳስ ወር ከአፍሪካ መሪዎች ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ ፋሽስት አብይ አሕመድ እንዳይሳተፍ ተስማምተዋል፡፡

Amnisty international and human rights wotch በጋራ ይፋ ባደረጉት የምርመራ ውጤት የፋሽስቱ አብይ ቡድን፡ የአማራ ተስፋፊ ሃይልና የአምባገነኑ ኢሳያስ ወታደሮች በጋራ በትግራይ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀልን ጨምሮ በሰብአዊነት ላይ ያነጣጠረ ወንጀል እንዲሁም በሴቶች ላይ ዘግናኝ የጅምላ ወሲባዊ ጥቃት መፈፀማቸው ማረጋገጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

የዴሞክራትና የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት በጋራ ውሳኔ በአንድ ድምፅ ረሃብን እንደጦር መሳሪያ በመጠቀም ሰላማዊ ሰዎች ላይ የምግብ እጥረት እንዲያጋጥም እየሰሩ ባሉት ፋሽስቱ አብይን ጨምሮ ለደቡብ ሱዳን፣ የመንና የሩስያ መሪዎች ግልፅ መልእክት ተላልፏል ተብሏል፡፡