የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ባለፉት ሶስት ሳምንታት የነበረዉን የጦርነት ዉሎ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ መንግስት ፀረ ሽምቅ ዘመቻ በማለት በመላዉ ኦሮምያ ላይ በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት እና በአንፃሩ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በርካታ የጦር መማረኩንም ገልጿል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ባለፉት ሶስት ሳምንታት የነበረዉን የጦርነት ዉሎ አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ አዉጥቶል፡፡ በመግለጫዉ በመንግስት ሃይሎች ላይ ከባድ ጉዳት እንዳደረሰ ገልፆ አያሌ የጦረ መሳሪያቸዉም እንደማረከ ሰራዊቱ አስታዉቆል፡፡ ሰራዊቱ በቦረና ዞን አሬሮ ወረዳ ከድሬ ወደ ሊበን ሲዘዋወሩ በነበሩ የመንግስት ሃይሎች ላይ በወሰደዉ እርምጃ አስር የፋሽስቱ ቡድን ወታደሮችን በመግደል አስራ አምስቱን ማቁሰሉን አስታውቆአል፡፡
በጉጂ ዞን ጎሮ አዶላ ወረዳ አዳዲ ከተማን ለመያዝ በተላኩ የአገዛዙ ሃይሎች ላይ ሰራዊቱ እርምጃ ወስዶ አስራ አንድ ገሎ አስራ ስድስቱን አቁሱሏል፡፡ በዚሁ ቀን ወደ አደዲ በተላኩ ተጨማሪ ሃይሎች ላይ እርምጃ ወስዶ ሃያ ሁለት የመንግስት ተዋጊዎች ሲገደሉ አስራ ሰባቱ ቆስለዋል ብሏል በመግለጫው፡፡
ሰራዊቱ በጉጂ ዞን ሰባ ቦሩ ወረዳ ልዩ ስሙ ስሬ ቡኪ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በሚንቀሳቀሱ የአገዛዙ ሃይሎች ላይ እርምጀ ወስዶ አስራ ስምንት ወታደሮች የገደለ ሲሆን አስራ አምስት የሚሆንትን ደግሞ ማቁሰሉ አስታዉቆል፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በዚህ ወረዳ በሎኮ ሁርቡ ኬሳ በወሰደዉ እርምጃ ስምንት የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ አስራ አምስቱ መቁሰላቸውን የገለፀው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በጉጂ ዞን ሊበን ለገ ጉላ በሚገኘዉ የምንግስት ወታደራዊ ካምፕ ላይ በወሰደዉ እርምጃ ደግሞ ሰባት ወታደሮች ሲገደሉ አስራ አንድ የሚሆኑት መቁሰላቸዉ አስታዉቆል፡፡
በጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ ዳርቻ ያባሰሬቲ በተባለዉ አከባቢ ሰፍሮ በሚገኘዉ የመንግስት ሃይሎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን ያስታወቀዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሃያ ሰባት ወታደሮች መግደሉንና የክፍለ ጦር አዛዡን መማረኩን ገልጿል፡፡ በዚሁ ዞን ዋድራ ከተማ የሚገኘዉ የአገዛዙን ወታራዊ ካምፕ በቁጥጥር ስር ማዋሉ የገለፀዉ ሰራዊቱ በእለቱ የወሰደዉ እርምጃ ሰባት የመንግስት ሃይሎች መገደላቸዉና ስምንት መቁሰላቸዉ አስታዉቆል፡፡
በጎሮ አዶላ ወረዳ የመንግስት ሃይሎች #አዳዲን ወረዳ ለመያዝ በርካታ ሰራዊት ካሰማሩ ቡሃላ በአዳ ቀራሩ ሲዘዋወሩ በነበሩ የመንግስት ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱ ሰራዊቱ አስታዉቆል፡፡ በዚህም አስራ ዘጠኝ የመንግስት ወታደሮች ተገለዋል፤ አስራ አንድ ደግሞ ቆስለዋል ነዉ የተባለዉ ፡፡ ከቆሰሉት መካከልም ዘጠኙ ህክምና እንዲያገኙ በሰራዊቱ ወደ ነገሌ ቦረና ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ ሂወታቸዉ ማለፉን ሰራዊቱ ጠቁሟል፡፡
በጉጂ ዞን ዋድራ ወረዳ በሃንዶይ ኪኖ በኩል በሚያልፈዉ የአገዛዙ ወታደር ላይ ሰራዊቱ በወሰደዉ እርምጃ አስራ ሁለት የመንግስት ሃይሎች መገደላቸው እና በአዶላ ሬዴ ወረዳ በአቡሉ ኡዱ በሚገኘዉ የአገዛዙ ሃይሎች ላይ በወሰደው እርምጃ ደግሞ አስር እንደገደለና ስምንቱን ማቁሰሉ በመግለጫዉ አስታዉቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ባለፈው ሶሰት ሳምንታት ዉስጥ በጉጂ ዞን ጉሚ ኤልደሎ ወረዳ በመልካ ለሚ፣ መልካ ጉባና መልካ ሩቃ በተደረጉ ጦርነቶች ድል መቀዳጀቱ አስታዉቋል፡፡ በነዚህ አካባቢዎች በተደረገዉ ውጊያ አንድ መቶ የመንግስት ሃይሎች መገደላቸዉን የገለፀዉ ሰራዊቱ ከሁለት መቶ በላይ ሰራዊቶች መቁሰላቸዉም አስታዉቋል፡፡ በርካታ ነፍስ ወከፍ የጦር መሳርያዎች እንደማረከ አስታዉቋል፡፡ ኮሎኔል ጨምሮ ሌሎች ወታደሮች ተማርከዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
በጉጂ ዞን ገላና ወረዳም መንግስት ባሰማራቸዉ ሃይሎች ላይም ድል መቀዳጀቱን ያስታወቀው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በዋድራ ወረዳ የአገዛዙን ወታደሮች በጫኑ አስራ አራት ተሽከርካሪዎች ላይ በወሰደው እርምጃ ሰላሳ አንድ ሲገደሉ ሰላሳ ሶስቱ ደግሞ መቁሰላቸዉ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን በመንግስት ሃይሎች ላይ በወሰደዉ እርምጃ ከመቶ በላይ ወታደሮቸ መገደላቸወን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ሰራዊቱ በምእራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረት ወረዳ የተካሄደዉን ዉጊያ ድል በማድረግ በፋሽስቱ ቡድን ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ አከባቢ ካስመዘገበው ድል በተጨማሪ ውልንጭቲ ቦሌና ዶን የተባሉ ከተሞችን መቆጣጠሩ የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ አስታዉቆል፡፡
መንግስት ፀረ ሽምቅ ዘመቻ በማለት ከሶስት ሳምንት በፊት በመላዉ ኦሮምያ ላይ ጦርነት መክፈቱ ተከትሎ በዚህ ጦርነት ላይ የፋሽስቱ ቡድን ሰራዊት፣ የአምባገነኑ #ኢሳያስ ቅጥረኛ ወታደሮች፣ የአማራ ተስፋፊ ክልል ሃይሎች፣ የፌደራል ፖሊስ ጨምሮ የኦሮሚያ ልዩ ሃይልና ሚኒሻ አቀናጅቶ እንዳሰማራ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ፍረወይኒ መንገሻ