Home ዜና የማህበራዊ ሚድያ ውሎ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች አቀባበል

የማህበራዊ ሚድያ ውሎ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች አቀባበል

630

በአሜሪካ በተካሄደው 18ኛ የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮን በድል ያጠናቀቁ ጀግኖች አትሌቶች እየተደረገ ያለው አቀባበል በበጎ ጎኑ  የሚታይ ቢሆንም የፋሽስት ቡድንን እና ግብረአበሮቹ  ግን ለፖለቲካ መጠቀሚያና ለህዝብ ስላቅ እያዋሉት እንደሆነ  ይስተዋላል፡፡

ሰሞንን በማህበራዊ ሚድያና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አነጋጋሪ የነበረው የ18ኛው የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮን የማራቶን አዲስ ክብረወሰን ባለቤት ጎይተቶም ገ/ስላሴ፣ በ10.000 ሜትር ርቀት የወርቅ መዳልያ አሸናፊ የአትሌት ለተሰንበት ግደይ እና  በአሜሪካ ኦሪጎን በአምስት ሺህ ሜትር ወርቅና ብር  ላጠለቀችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ

ለሃገራቸው እልፍ ከከፈሉ የትግራይ ተወላጆች  ወገኖቻቸው ተርታ  የሚስቀምጣቸው  ድል ማስመዝገባቸው  የማይካድ ሀቅ ነው፡፡

ጀግኖቹ የትግራይ ተወላጅ አትሌቶች በኦሪጎን ከተማ በድል ቢያሸበርቁም በቤተሰቦቻቸውና በትግራይ ህዝብ እየደረሰ ያለውን የጀኖሳይድ ጦርነት ግን ለአለም ማስተጋባት ከቶ አልቻሉም፡፡

ይሁን እንጂ  ሰሞኑን   ታዋቂ የፖለቲካ ተንታን  ማርቲን ፕሎውትን ጨምሮ   በርካታ አገር ወዳድ እና ህዝባቸውና ቤተሰቦቻቸው በችግሩ ሰለባ ለሆኑ ተጠቂ ዜጎች ባገኙት አጋጣሚ የፋሽስቱ ቡድን እና ግብረ አበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ እካሄዱት ባለው  የጀኖሳይድ ጦርነት ድምፅ ላላገኙት ድምፅ ለመሆን ሁነቱ ሲጠቀሙበት ተስተውለዋል፡፡

በዛሬው ቀን ከተስተጋቡትና  የትዊተርና የማህበራዊ ሚድያ ትኩረት ከሳቡት እና እወነታውን ከገለፁት የሳሙኤል በቀለ እና የሰይፈስላሴ  ገብረመስቀል መልእክቶች ይጠቀሳሉ፤  የእውቁ ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባ ልጅ ሳሙኤል  በቀለ የትግራይና የኦሮሞ  አትሌቶች ድል “የሁላችን ድል ነው” ፤ የትግራይና የኦሮሞ ህዝብ ችግር ሲሆን ግን” የራሳቸው ጉዳይ ነው “መባሉን ተችተዋል፡፡

 ቀጥሎም ድል ሲያስመዘግቡ “ጀግኖች “፤ መብታቸው ሲጠይቁ ደግሞ “ፅንፈኞች ” የሚለውን  የትዊትር መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በፋሽስቱ ቤተመንግስት ለተደረገው አቀባበል ጀግኒት ጎይተይቶም ገብረስላሴን በሃገርዋና ቤተሰቦዋ እየደረሰ ባለው ግፍና መከራ የተነሳ    በእንግዳ መቀበያው ገብታ አምባዋን መቆጣጠር እንዳቃታትና  አምርራ  እንዳለቀሰች  በዚህም ስለ ቤተሰቦችዋ ሁኔታ ለ20 ወራት በከበባና ክልከላ ምክንያት ስላሉበት ሁኔታ  ማወቅና መስማት አለመቻልዋ ነው ያስታወቀው፤ ሰይፈስላሴ  ገብረመስቀል

 በፋሽስት ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ባለው የጀኖሳይድ ጦርነት ማአርግ መኮነን የውጭ አገር ጋዜጠኞች ላቀረቡለት ጥያቄም ላለፉት አመታት የትግራይ ህዝብ ኢትዮጵያን የገነባ መሆኑን ተዘንግቶ በፋሽስቱ ቡድንና ግብረአበሮቹ በላዩ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል እየተፈፀመበት ይገኛል ማለቱ ይታወሳል፡፡

ሃይለኪሮስ ወልዳይ