Home ዜና የማህበራዊ ሚድያ ውሎ

የማህበራዊ ሚድያ ውሎ

542
0

ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጓች ድርጅቶች Humanrightswotch and Amnesty international በጋራ ይፋ ባደረጉት አዳዲስ ሪፖርቶች በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እጅግ አነጋጋሪ ሆነው ውለዋል፡፡የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች ትግራዋይን ከዚህ ምድር ለማጥፋት የፈጸማቸው አሰቃቂ ግፎች እና የጥፋት አሻራቸውን ለማጥፋት የተጠቀሙበትን ተንኮል በተለያዩ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና አለም አቀፍ ሚድያዎች ከፍተኛ ውግዘት እየደረሰበት ነው፡፡

የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊትና የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች ኤርትራውን ወያኔን በማጥፋታችው መኩራት አለባችው ሲሉ በትግራይዋይ ሞት ደስታቸውን ለመግለጽ በሁመራ የሙዚቃ ድግስ ማቅረባቸውን ብዙዎችን ያስገረመ ሆኗል፡፡የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች ተጋሩ ለማጥፋት የተጠቀሙበት ጭካኔ የተሞላበት ግድያና ሰብአዊ ጥሰት በተለያዩ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተማጋቾች እና የአለም አቀፍ ሚድያዎች ዛሬ በማህበራዊ ሚድያ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል፡፡

የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች በምዕራብ ትግራይ የፈጸሙትን ግፍ የሚያሳይ የካርቶን ምስል የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ሆኖ ውላል፡፡ስእሉ ላይ እንደሚታየው ተስፋፊ ሀይሎች የተጋሩ ተወላጆችን ትግሬዎች ውጡ የሚል ባነር አስይዞ አፈሙዝ ደግኖ በግድ ማንነታቸውን ለማስቀየር ሲሞክሩ፤ የትግራይ ተወላጆች ደግሞ ከሞት ለማምለጥ ሲሉ በግድ ባነሩን ሲያነሱና የራሳቸውን ያልሆነ ማንነት ለመቀበል ውሳጣቸው እየከነከናቸው በከፍተኛ የሀዘን ስሜት ተውጦ የሲቃ እንባ ሲያነቡ ያሳያል፡፡

በምዕራብ ትግራይ ይኖሩ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ከአስራ አምስት እስከ አርባ አምስት እድሜ ያሉት በግፍ እየረሸኑ ወደ ተከዜ ወንዝ ሲወረውራቸው የቀሩቱን ደግሞ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ተከዘን አሻግሮ ሲልካቸው የሚያሳይ የካርቶን ስእልም ላለፉት አስራ ስድስት ወራት ሲሰራ የነበረ ግፍ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ በመሆኑ ብዙዎችን ሲቀባበሉት እና በማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ዘንድ የተለያየ አስተያየት ሲሰጥበት ውለዋል፡፡

የአማራ ልዩ ሀይል አባላት ወደ 60 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆችን የተከዘ ድልድይ ጋር ወስደው ረሽኖዋቸዋል፡፡ ጭፍጨፋውና ግፉ አሁንም እየቀጠለ በመሆኑ አለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ሀይል በቦታው አንዲሰማራም አለም አቀፍ የመብት ተማጓቾች ጠይቀዋል

፡፡እነዚህ የመብት ተማጓቾች በምዕራብ ትግራይ የትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመ ወንጀል በማስመልከት የምስራቅ አፍሪካ የሂዮማን ራይትስዎች ዳይሬክተር ላትሻ ባድር ሪፖርቱን አስመልክታ በማህበራዊ የትስስር ገጻ ባሰፈረችው ጽሁፍ የአማራ ሀይሎች ላለፉት አስራ ስድስት ወራት ካለ እርፍት ትግራዋይን የማጽዳት ስራ ሲሰሩ እንደነበር የሚያጋልጥ ዶክመት ነው በማለት ጽፋለች፡፡

የፋሽስቱ ሰራዊት ከአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት በትግራይ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ስለመፈጸማቸውና እና በሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራዋይ እንስሳት እንደዘረፉም በማህበራዊ የትስስር ገጽዋ አጋርታለች፡፡የአማራ ተስፋፊ ሀይሎችና የፋሽስቱ ቡድን በምዕራብ በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከዚህ ምድር እናጠፋችዋለን በሚል ዘመቻ የሰሩትን ግፍ ለማጥፋት ቢሚክሩም እውነታው ግን የአለም ሚድያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እየመሰከሩ ነው፡፡ኢትዮጵያ በተጋሩ ላይ ለፈጸመችው ወንጀል ቅጣትዋ ማግኘት አለባቸው ሲል የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ ማርቲን ፕላውት ጽፏል፡፡

ካሳ ሀይለማሪያም የአማራ ሀይሎች መረጃን ለማጥፋት እየሰሩት ያለውን ሴራ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲሰጠው ሲል የትግራይ ውጭ ጉዳይ የሰጠውን መግለጫ በመለጠፍ በትስስር ገጹ አጋርቷል፡፡ TheGlob and male በበኩሉ በምዕራብ ትግራይ የተጋሩን ዘር ለማጥፋት ሲካሄድ የነበረው ቅስቀሳ ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጫ ተገኘ በሚል ያሰራጨው ዘገባም ብዙዎችን እየተቀባበሉት ነው፡፡

ትግሃት ሚድያ የአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ሰራዊትና እና የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች ትግራዋይን ለማጥፋት የሰሩበትን አሳፋሪ ድርጊት ለማስታወስ እና ዳግም ወረራ ለመፈጸም በሁመራ የሙዚቃ ድግስ ማድረጋቸውን ጽፏል፡፡ኤርትራዊ ወያኔን በማጥፋትህ ኩራ በማለት አሳፋሪ ድርጊታቸውን በአደባባይ መስክረዋል፡፡

ፍቅር ያሸንፋል እያሉ በሌላ በኩል ደግሞ በጋራ ሁነን ትግራዋይን ከዚህ ምድር እናጠፋለን በማለት የታወረ ጥላቻቸውን በመድረክ ሲያቀርቡ ተስተውሏል፡፡በአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ በከንቱ ምኞት ኤርትራን የአፍሪካ ሲንጋፖር እናደርጋታለን ብሎ የአፍሪካ ሰሜን ኮርያ ያደረጋት አገር ላለፉት 30 አመታት የኤርትራ ወጣቶች በማያውቁት ጦርነት እያስገባ እንዳላስጨረሳሸው ሁሉ መድረክ መሪው ግን ስለየተኛዋ አገር እያወራ እንደሆነ የገባው አይመስልም በማለት ብዙዎቸን ሀሳባቸውን በትስስር ገጾች አስፍረዋል፡፡

Previous articleበማዳበርያ ዋጋ መናር̎ ምክንያት መሬታችን ምንም አዝርዕት ሳይዘራበት ሊከርም ይችላል ሲሉ አርሳደሮች ስጋታቸው ገለፁ
Next articleየትግራይ ውጭ ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ