Home ዜና “የምዕራባውያን የዲፕሎማሲ ውድቀት በትግራይ ጦርነት“ ማርቲን ፕላውት

“የምዕራባውያን የዲፕሎማሲ ውድቀት በትግራይ ጦርነት“ ማርቲን ፕላውት

2066

—–

የአፍሪካ ቀንድ እና የደቡብ አፍሪካ ጉዳዮች የሚከታተለው ጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውት “የምዕራባውያን የዲፕሎማሲ ውድቀት በትግራይ ጦርነት“ በሚል ርእስ ባጠናቀረው ሃተታ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ሰራዊት ላይ እንደ አዲስ በከፈተው የጦርነት ማእበል በአለም አቀፍ ታዛቢዎች ዘንድ አዲስ ዙር ዘር የማፅዳት እና የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሊከሰቱ ይችላሉ የሚል ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልጿል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በዚህ ሳምንት በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መጥቷል፣ ማሕበራዊ መስተጋብሮች ተበጣጥሰዋል በዚህም ሰላማውያን ዜጎች አስደንጋጭ ዋጋ እየከፈሉ ናቸው“ ማለታቸውን ያስታወሰው ሐተታው ማክሰኞ እለት ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሽረ ከተማን እንደተቆጣጠረ ያስነገረ ቢሆንም ብርቱ ተፋላሚው የትግራይ ሰራዊት ምናልባትም ግዚያዊ የማፈግፈግ ስልት ተጠቅሞ በመጪዎቹ ቀናት ወይም ሳምንት ውስጥ መልሶ ማጥቃት ሊጀምር እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፡፡

አደገኛው ነገር ይላል የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ተንታኙ ዊልያም ዳቪሰን አደገኛው ነገር ግዙፍ መጠን ያለው የትግራይ ሰራዊት ጥምር ወራሪ ሐይሎቹን መመከቱን አጠናክሮ ከቀጠለ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች ይህንን የምከታ መንፈስን ለመስበር ሲሉ ሰላማውያን ዜጎችን ሊጨፈጭፉ ይችላሉ ሁኔታው አስፈሪ ነው ሲል ገልፆታል፡፡

ትግራይ በአለማችን አስከፊ የሚባል ጦርነት እያስተናገደች ቢሆንም የአለምአቀፍ ትኩረት በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ላይ በማነጣጠሩ ምክንያት ግን የትግራይ ጦርነት በሰፊው ተዘንግቷል የሚለው የማርቲን ፕላውት ሐተታ፣ ከጥቅምት ወር 2013 ዓ/ም የጀመረው አስከፊው ሰብአዊ ቀውስ ከአምስት ሚልዮን በላይ ህዝብ ለረሃብ አጋልጦታል፣  በከበባው ምክንያት ትግራይ ከተቀረው አለም ተቆራርጣለች ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በመሰረታዊ አገልግሎቶች እና ሸቀጦች ላይ በጣለው ክልከላ ምክንያትም ሰላማውያን ዜጎች ምግብ፣ መድሃኒት፣ የባንክ እና የስልክ አገልግሎቶች ማግኘት አልቻሉም፤ በትግራይ ያለውን ሁኔታ በተመለከተም አለምአቀፍ ጋዜጠኞች ነፃ ሁነው መዘገብ አይችሉም ሲል አትቷል፡፡

በትግራይ ጦርነቱ ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ ዲፕሎማቶች፣ መንስታዊ ያልሆኑ አለምአቀፍ ተቋማት እና ምሁራን ሊከሰት ስለሚችለው የኢትዮጵያ የመበታተን አደጋ ሲያሰጋቸው ነበር የሚለው የማርቲን ፕላውት ሐተታ፣ ሆኖም የቀጠለው ክስተት በሃገሪቱ ከፍተኛ ግጭትን ከማስተናገድ አልፎ በታሪክ የቀጠናው አጎራባች ሃገሮችን በማረጋጋት ረገድ ቁልፍ ሚና ስትጫወት የነበረችው ሃገር አሁን ላይ የቀጠናው መረጋጋት አውካዋለች እስካሁን የተሞከሩ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችም ቢሆኑ ውጤት አልባ ነበሩ ብሏል ማርቲን ፕላውት በሐተታው፡፡

በቅርቡ የተቀረው አለምን ጫካ በማለት የወረፉት  የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፍ ቦሬል  ስለጦርነቱ እስካሁን ያልተሰማ ግልፅ ትችትን ሰንዝረዋል በተደጋጋሚም ፋሽስቱ የአብይ ቡድንን ሲያጣጥሉ ተሰምተዋል የሚለው ሐተታው ይሁንና ከብራስለስ የተሰማውን የጆሴፍ ቦሬል የዲፕሎማሲ ድምፅ አንዳንድ የአውሮፓ ሕብረት ባለስልጣናትን አላስደሰተም ምክንያታቸውም በፋሽስቱ ቡድን በኩል ለህወሓት ታዳላላችሁ የሚል ምልከታ እየተፈጠረ ጥረታችን ከንቱ እያደረገብን ነው በማለት ወቀሳቸውን ያሰማሉ ሲል ማርቲን ፕላውት በሐተታው አመላክቷል፡፡    

በብራስለስ የሚገኘው በአውሮፓ የትግራይ መንግስት ተወካይ መርከብ ነጋሽ ይመሰል አዲሱን የፋሽስቱ ቡድን ዘመቻ ጀኖሳይድ በማለት ይገልፀዋል፣ ጥምር ወራሪ ሐይሎቹ ሰላማውያን ዜጎች ቀዮቸውን እንዲለቁ በማስገደድ በተፈናቃይ መጠለያ ጣብያዎች እንዲጠለሉ እያደረግዋቸው ነው ይላል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ  የጀኖሳይድ ግባቸው የትግራይ ህዝብን ማጥፋት ነው፣ የአዲሱ ጥቃት መሰረታዊ አላማም የትግራይ ህዝብን ማሕበራዊ መሰረቶች መናድ ነው፣ ለዚህም ነው በትግራይ ከ3 ሚልዮን የሚበልጥ ህዝብ  ለማፈናቀል አቅደው እየሰሩ ያሉት ብሏል፡፡

ሌላው ማርቲን ፕላውት በሐተታው ያካተተው የፕሮፌሰር መሐሪ ታደለ ማሩ ሐሳብን ነው፡ ፕሮፌሰር መሓሪ የትግራይ ጉዳይ በ1986 ዓ/ም በሩዋንዳ በቱትሲዎች ላይ ከተፈፀመው ጀኖሳይድ ጋር በማነፃፀር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንደምክንያትም የጥምር ወራሪ ሐይሎቹ እቅድ በተቀላጠፈ መልኩ የትግራይ ህዝብን ቁጥር መቀነስ ነው፣ ይህም የትግራይ ዘርን ለማጥፋት የያዙት እቅድ አካል ሆኖ በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል እና የጦር ወንጀልም ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም በበኩላቸው በትግራይ ህዝብ ላይ ያንዣበበው ጀኖሳይድ እንደሚያሰጋቸው በገለፁበት የአለም ማሕበረሰብ የትግራይ ጉዳይ የሚገባውን ትኩረት አልሰጠውም አሁን ላይ በትግራይ ጀኖሳይድ እንዳይፈፀም ለመከላከል በጣም ጠባብ እድል ነው ያለው ማለታቸውን በሐተታው ተመላክቷል፡፡

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የምዕራቡ ዓለም ዲፕሎማት እንዳሉትም ኢትዮጵያና ኤርትራ የትግራይ ህዝብ ለሰራዊቱ ድጋፍ እንዳያደርግ የማጎርያ ካምፖች ለማዘጋጀት አቅደዋል፣ ይህም የትግራይ ሰላማውያን ዜጎች ከቤታቸው በማውጣት ወደ ተፈናቃዮች ካምፕ እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ስሌቱም የትግራይ ህዝብ በመጪዎቹ አመታት ከፖለቲካው ትግል ለማግለል ነው ሲሉ የጥምር ወራሪ ሐይሎቹ ሚስጥራዊ እቅድ ገሀድ አድርገውታል፡፡

የትግራይ ህዝብን በፖለቲካ ትግሉ ምንም ትርጉም የሌለው ተሳትፎ እንዲኖረው ያለመ ሴራ እንደሆነ ያመላከተው ማርቲን ፕላውት፣ ትልቁ ስጋት ምዕራባውያን በዚሁ ህዝቡን አስገድዶ በማጎርያ ካምፖች የማስፈር እቅድ ግብረአበሮች መሆናቸውን ነው፡፡ የሚፈናቀሉትን በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የረድኤት ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወን ፕሮጀክት መሆኑን ነው ብሏል፡፡

ሌላ የአውሮፓ ዲፕሎማትም ይህንን የማጎር እቅድ ተግባራዊ የመደረጉን ጉዳይ በተመለከተ ሐሳባቸውን አጋርተዋል፣ በትግራይ ያለው ሁኔታ ያስፈራል፣ ይህም የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የዲፕሎማሲ ውድቀት ነው ብለዋል፡፡

የወርልድ ፒስ ፋውንዴሽን ዋና ዳይሬክተር የሆነው አሌክስ ዲዋልም የአሜሪካ፣ የተባቡሩት መንግስታት፣ የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ትግራይን የካዱ ሲል ይተቻል፣ በአውሮፓ የትግራይ መንግስት ተወካይ መርከብ ነጋሽ ይመሰል በበኩላቸው አለምአቀፉ ማሕበረሰብ የከፋ ሰብአዊ ቀውስ እያስተናገደ ያለው በሚልዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ለመታደግ ሐላፊነቱን ላለመወጣት ሲል በትግራይ እየሆነ ስላለው ነገር እውቅና መስጠት አይፈልግም ብሏል፡፡ እዚህ ላይ የምዕራባውያን ሙሉ በሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ውድቀት ወይስ ይህን እንዲፈፀም መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ የሚለውን እርግጠኛ አይደለሁም ያለበትን ሐሳብ በማካተት ማርቲን ፕላውት ሐተታውን አጠቃሏል፡፡