Home ዜና የትግራይና የአገው ህዝብ የዘመናት ታሪካዊና ማህበራዊ ግንኙነት ለመበጣጠስ የሚሞክሩ ሃይሎችን በጋራ መመከት...

የትግራይና የአገው ህዝብ የዘመናት ታሪካዊና ማህበራዊ ግንኙነት ለመበጣጠስ የሚሞክሩ ሃይሎችን በጋራ መመከት እንደሚገባ ተገለፀ።

1027

የትግራይና የአገው ህዝብ ለዘመናት ኣብሮ የኖረና የተዛመደ ሰፊ ማህበራዊ  መስተጋብር ያላቸው ህዝቦች ናቸው፡፡

እነዚህ ህዝቦች በአንድ ክንድ በመሆን ቀደምት ጠላቶችን በመደምሰስ አብረው ሲዋደቁ የመጡ ሲሆን አሁንም ፋሽስታዊያን ጠላቶች ዳግም የትግራይና የአገው ህዝብን  ለማንበርከክ እየፈፀሙት ያለውን ግፍ እንደ ቀደመው ታሪካቸው አሁንም በጋራ ተሰልፈዋል፡፡

ይህን የሁለቱን ህዝቦች የጋራ ትግልና አብሮነት የበለጠ የሚያጠናከር ህዝባዊ ኮንፈረንስ በደቡብ ትግራይ ዞን በቦራ ከተማ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ የተገኙት የትግራይ ደቡባዊ ዞን ኣስተዳዳሪ ታጋይ ሃፍቱ ኪሮስ  እንዲሁም የአገው ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ  ሊቀ መንበር ታጋይ ኪሮስ ሮምሃ  የሁለቱን ህዝቦች ታሪካዊ ትስስር እና አሁናዊ አብሮነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሁለቱም ህዝቦች እያካሄዱት ያለው ፍትሃዊ ትግል አላማ እና ህዝባዊ መርህ የያዘ መሆኑን በኮንፈረንሱ ላይ አብራርተዋል፡፡

በህዝባዊው ኮንፈረንስ ላይ  የተገኙት የሁለቱም ህዝቦች ተሳታፊዎች  የፋሽስቱ ቡድንና የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊቶች የትግራይንና የኣገው  አካባቢዎች በቆዩባቸው ወቅት በህዝብ ላይ የፈፀሙት ግፍ ተናግረዋል፤ 

እነዚህ ደመኛ ጠላቶችንም በጋራ መመከት ይገባናል ሲሉም አክለዋል፡፡

 ፍረሂወት ተ/መድህን