Home ዜና የትግራይን ህዝብ ከተጣለበት ክልከላ ለመውጣት ሌላኛውን አማራጭ እንዲጠቀም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ሊታሰብባቸው ይገባል...

የትግራይን ህዝብ ከተጣለበት ክልከላ ለመውጣት ሌላኛውን አማራጭ እንዲጠቀም የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ሊታሰብባቸው ይገባል ተባለ፡፡

571

—–   

አለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ በፋሽስቱ ቡድን ላይ ተግባራዊ እርምጃ አለመውሰድ እና የሚያሳየው መለሳለስ የትግራይን ህዝብ ሰቆቃ ያላገናዘበ ነው ሲሉ የትግራይ መንግሰት ኮሙዮኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሐላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም አስታወቁ።

አቶ ረዳኤ ከዝግጅት ክፍላች ጋር በነበራቸው ቆይታ ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የጣለው ከበባ በቀጠለበት ሁኔታ የአለም ባንክ ይሰጣል የተባለው ገንዘብ ፋሽስቱ ቡድን ከጥፋቱ እንዳይታረም የሚያደርግ በአንፃሩ የትግራይን ህዝብ ስቃይና ሰቆቃ እንዲራዘም ጦርነቱም እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በመሆኑም እንደዚህ አይነት እርምጃዎች የትግራይን ህዝብ ከተጣለበት ክልከላ ለመውጣት በሰላማዊ ሂደቱ ላይ የነበረው ተስፋ እንዲቆርጥ እና ሌላኛውን አማራጭ እንዲጠቀም የሚያስገድድ መሆኑን አስገንዝበዋል።