Home ዜና የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ህዝብን የቅርስ ዘረፋና ውድመት ——

የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ህዝብን የቅርስ ዘረፋና ውድመት ——

852

የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የትግራይ ህዝብ ታሪክ እና ቅርስ በመዝረፍ ባለ ቤት ለመሆን ካላቸው ጉጉት የተነሳ በትግራይ የሚገኙ አብያተ ክርስትያናት የቻሉትን ዘርፈው ያልቻሉትን ማውደማቸውን ተገለፀ፡፡
ትግራይ ጥንታዊ ሀይማኖታዊ ቅርሶች ባለቤት ናት፤ ይህ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ማንነት መገለጫ መሆኑን የመቐለ ማህደረ ስብሀት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ካቴድርያል ዋና አስተዳዳሪ መጋቢ ስብሀት ጌራወርቅ ተስፋይ ይገልፃሉ፡፡
የትግራይ ህዝብ ታሪካውያን ጠላቶች በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀሙት ያሉት ጆኖሳይድ የትግራይን ህዝብ እንደዘር አጥፍተው የትግራይን ህዝብ ታሪክ እና ቅርስ ለመዝረፍ አቅደው እና ሆን ብለው የሰሩት ወንጀል እንደሆነ መጋቢ ስብሀት ጌራወርቅ ያብራራሉ፡፡

መጋቢ ስብሀት አክለውም የትግራይ ቤተ ክህነት መመስረቱ የትግራይን ታሪክ እና ቅርስ ለመጠበቅ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በመግለፅ የትግራይ ህዝብ የራሱ የሆነውን ታሪክ እና ቅርስ መጠበቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል ፡፡የትግራይን ህዝብ እውነተኛ ማንነት የሚገልፁ ታሪኮች ባህለዊ እና ሀይማኖታዊ ይዞታቸው ሳይበረዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ በሚገባ ሊያዙና ሊጠበቁ እንደሚገባም ነው የሚያስረዱት፡፡
ትግራይ የሀይማኖታዊ ይዘት እና የሀይማኖታዊ ቅርሶች ባለቤት እንደሆነች በከተማ እና በገጠር በተለይ ደግሞ በገጠር አካባቢዎች በርካታ ውቅር አብያተ-ክርስተያናት በሀወልት፣ በተለያዩ ድንጋዮች እና በብራና የተፃፉ ፅሁፎቻችን የያዘች የቅርሶችን መፍለቅያ ስትሆን አብዛኞቹም ሀይማኖታዊ ይዘት ያለቸውእንደሆኑ፤ ቤተ-ክርስትያኒቱ እንዚህን ቅርሶቸን በሚገባ ጠብቃ ሀይማኖታዊ ትውፊት እና ይዘት ሳይሸራረፍ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ አድርጋለች፡፡

በተጨማሪም በቅዱስ ያሬድ ያለውን ትውፊት በተጠናከረ መልኩ ወደ ዜማ የሚቀየርበት አካሄድ ነው እያየን ያለነው ሲሉም አስተያየታቸው ገልፀዋል፡፡
ዘመናዊ ተክኖሎጂ ተጠቅመው ከውጭ ሀይሎች ጋር በመተባበር ጠላቶቻችን በቅርሶች ውድመት አካሂደዋል፡፡

የነዚህ የጥፋት ሀይሎች እኩይ አላማ የትግራይ ህዝብ አጥፍተህ የትግራይን ህዝብ መለያ የሆኑ ታሪኮችን በመዝረፍ የኛ ታሪክ ነው ብለው ለመውሰድ እንደነበረ ተጋልጠዋል፡፡
የአክሱም መንበረ ሰላማ ወደ ባለቤቱ እና ወደ ቦታው እንዲመለስ የትግራይ ቤተ-ክህነት እየሰራች ትገኛለች፡፡ ስለሆነም የትግራይ ህዝብ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ነቅቶ ሊሰራ ይገባል በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡