ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈተዉ የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ዉጭ ሆነው ለስነ ልቦናዊ ጉዳቶች መዳረጋቸውን #ህፃናት ተማሪዎች ተናገሩ፡፡
በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰው ሰዉ ሰራሽ ርሃብ እና ቀውስ እንዲያበቃ ለአለም ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፋሽስቱ ቡድን የትግራይን ህዝብ እንደ ህዝብ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት የነበራቸዉ ፍላጎት ያልተሳካላቻዉ ቢሆንም ፋሽስታዊ ወራሪዎች የትግራይን ህዝብ ለማዳካም ለረጅም ግዜ አቅደዉ በትኩረት ከሚንቀሳቀሱባቸው መካከል የትምህርት ዘርፍ ማውደምና የመማር ማስተማር ሂደት ማስተጓጎል አንዱ ነዉ፡፡ ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ በከፈተዉ የጀኖሳይድ ጦርነት ሳቢያ ትምህርት ቤቶች እንዲወድሙና ተማሪዎች ከትምህርት ማእድ እንዲርቁ ተደርገዋል፡፡ በዚህም የትግራይ ህፃናት ከትምህርት ገበታ ዉጭ እንደሆኑ መደረጋቸዉ በመቐለ ከተማ የሚገኙ ህፃናት ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡
የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ባለው ጀኖሳይድ ትግራይንና ህዝቧን ወደኋላ ለመመለሰና ተተኪ ትዉልድ እንዳይፈጠር ታልሞ የተሰራ ድርጊት በመሆኑ እነዚህ ህፃናትም በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጠረዉ ከበባና ክልከላ ምክንያት ለርሃብ እንደተጋለጡ በህፃን አንደበታቸዉ ይናገራሉ፡፡
ህፃናቶቹ አክለዉም ወራሪ ሃይሎች ከትግራይ መሬት ለቀዉ እነዲወጡ ፣ ጦርነት እንዲያቆምና በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጠረዉ ሰዉ ሰራሽ አደጋ እንዲቆም የአለም ማህበረሰብና የህፃናተ መብት ተሞጋቾች ሊያግዙን ይገባል ብለዋል፡፡
በተለያየ የክፍል ደረጃ የሚማሩ ተማሪዎች እንደገለፁት ትምህርት መማር አልቻልንም ምክንያቱ ትምህርት ቤቶቹ ወድመዋል በከበባዉና በክልከላዉ ምክንያትም ተርበናል፡፡ ትምህርት ቤታችን በመዉደሙና በመሰረቁ ምክንያት መማር አልቻልንም ብለዋል፡፡ እኛ ህፃናት ሁለት አመት ትምህርት በመቋረጡና በርሃብ ምክንያት ከባድ ችግር ነዉ ያሳለፍነዉ፡፡ አሁንም በትግራይ ህዝብና በህፃናት ላይ እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ በቃላት የምትገልፀዉ አይደለም፡፡
አብይ አህመድ በድሮን እየደበደበን ስለነበር ከቤት አንወጣም ነበር አሁን ነዉ ከቤተ መዉጣት የጀመርነዉ፡፡ አሁንም ቢሆን ምግብ ሳንበላ ነዉ የምናድረዉ አብይ አህመድ በከበባና በክልከላ ዉስጥ ስላስገባን ምግብ ማግኘት አልቻልንም ካገኘንም ትንሽ ነዉ የምንበላዉ፡፡
ያለ ምግብ መንቀሳቀስ ስላልቻልን በጣም ተርበናል በቃ አቅም አጥተናል፡፡ በትግራይ ከባድ ርሃብ ነዉ ያለዉ ምንም ማድረግ አልቻልንም፡፡አብዛኛው በስደትና በርሃብ ዉስጥ ነዉ ያለዉ የአለም ማህበረሰብ ያለንበትን ችግር ተረድቶ ሊያግዘን ይገባል፡፡
እኛ ህፃናት የነገ ሃገር ተረካቢዎች ስለሆን ተስፋ እንድናደርግ ምግብና የተለያዩ ነገሮች ልናገኝ ይገባል፡፡ በትግራይ ብዙ ህዝብ በችግር ዉስጥ ነዉ የሚገኘዉ በተለይ ደግሞ ለከባድ ርሃብና በሽታ የተጋለጡ ብዙ ህፃናት ስላሉ የአለም ማህበረሰብና የህፃናት መብት ተሞጋች ሊያግዙን ይገባል፡፡ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡