Home ዜና የትግራይ መንግስት 31ኛ ዓመት የግንቦት 20 ክብረ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው...

የትግራይ መንግስት 31ኛ ዓመት የግንቦት 20 ክብረ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ

712

የህዝብ ሉአላዊነት አስደፍሮ ከብርሃን ወደ ጨለማ ከልማት ወደ ጥፋትና እልቂት ያሸጋገረ፤ የአራት ኪሎው ቤተ መንግስት አገዛዝ ተጠያቂ የሚሆንበት ወቅት አሁን ነው ሲል የትግራይ መንግስት አስታወቀ፡፡

የትግራይ መንግስት 31ኛ ዓመት የግንቦት 20 ክብረ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ ግንቦት 20 በየዓመቱ የምናከብረው አሃዳዊ አገዛዝ ከነግሳንግሱ በመመንገል እያንዳንዱ ዜጋ የነፃነት አየር እየተነፈሰ በእኩልነት የተመሰረተ ብዙህነትና ልዩነት ፀጋ መሆኑን በ27 አመታት የሚዳሰስና የሚጨበጥ ውጤት እንዲመዘገብ መሰረት የተጣለበት እለት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

የአፄ ሚኒሊክ ፕሮጀክት የሆነውን የአሃደዊ አስተሳሰብ አቀንቃኝ ፋሽስት አብይ አሕመድ ቡድን ከ19 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የተሳተፈበትና በተወካዮቹ ያፀደቀው ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ  ፌደራላዊ ስርዓቱ በጉልበት በመደፍጠጥ ለዚህ ሁለንተናዊ የድል ምንጭ የሆነችውን ግንቦት 20 ላለፉት አራት ዓመታት በአደባባይ እንዳትከበር አድርጓል ብሏል መገለጫው፡፡

ኢትዮጵያና ህዝቧቿ ከብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማ ከልማት ወደ ጥፋት  ከቀድሞ ዩጎዝላቪያ በከፋና ለመተንበይ አስቸጋሪ ወደ ሆነው መጠፋፋትና ብተና አፋፍ ላይ እንዳደረሳት መግለጫው አመልክተዋል፡፡

የፋሽስት አብይ አሕመድ ቡድን የቀድሞ ኢህአደግ አገሪቱን ያስተዳደረባቸው 27 ዓመት የጨለማ ዓመታት ነበሩ በማለት የኤርትራው አምባገነኑ መንግስትና የትላንቱ የአፄዎቹና የፋሽስት ወታደራዊ ደርግ አገዛዝ ናፋቂዎች ፍላጎትና ምኞት ለማሳካት ሲል የነበረው ብሩህ ተስፋ ጉዞ በተውገረገረ ቃላት የጨለማ ግርዶሽ ለማልበስ ቢሞክርም እውነቱን ግን ከቶውም ሊቀይረው አይችልም ብሏል፡፡

ፋሽስት አብይ ቡድን አይኑን በጥቁር ጨርቅ ሸፍኖ ያለምንም ይሉኝታ ኢህአደግ ገንብቶ ወደ ማጠናቀቅ ደራጃ አድርሷቸው የነበሩትን ለኢትዮጵያ ህዝብና ለድፍን ዓለም  ያማለሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ከመጎብኘትና ሪቫን ከመቁረጥ የዘለለ ስራ ለመስራት  አልቻለም ብሏል፡፡

ፋሽስቱ አራት አመታት ሙሉ የአገሪቱን አንጡራ ሀብት ለስነ-ልቦና ውግያ እና ትርጉም የለሽ ደም አፋሳሽ ጦርነት አውሎ አገሪቱ የትርምስ አውድማ በማድረግ እማትወጣበት መቀመቅ ውስጥ ከቷት ይገኛል ብሏል የትግራይ መንግስት መግለጫ፡፡

የሰላም ተምሳሌትና በአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተግባር በቀዳሚነት ይሰለፉ ከነበሩት ሃገራት ተጠቃሽ የነበረችው ኢትዮጵያ የፋሽስት ቡድኑ በአራት አመታት የስልጣን ጊዜው የፌደራል ስርዓቱን በጉልበት ንዶ ህግና ስርአት ጠፍቶ ሃገሪቱ መረጋጋትና ሰላም ርቋት የጎበዝ አለቆችና የወሮ በሎች መፈንጫ  እንድትሆን ኣድረጓታል፡፡

ዜጎቿ በጠራራ ፀሃይ በአደባባይ የሚዘረፉባት የሚደበደቡባት በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች በየእስር ቤቱና ጉራንጉሩ የሚታጎሩባት ተጨፍጭፈውም የሚገደሉባት ሃገር ሆኖለች  ብሏልመግለጫው፡፡

ኢትዮጵያ በፋሽስት የአብይ ቡድን የስልጣን ዘመን የዓለም ባንክ የአገሪቱ ኢኮኖሚ መተንበይ የተቸገረበት በአገር ውስጥ ህዝቦች በማፈናቀል ቀዳሚ ደረጃ የያዘችበት በአጭሩ ፋብሪካዎች ተዘግተው የስራ አጥ ቁጥር በእጥፍ ድርብ የጨመረበት እንዲሁም በአራቱም አቅጣጫዎች የራሳቸውን እድል በራስ ለመወሰን ነፍጥ አንስተው የፋሽስቱን ቡድን የሚፋለሙ የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የአፋር፣ የቅማንት፣ የአገውና ሌሎችም ታጋይ የአርነት ሃይሎች ትግላቸውን በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች እየተካሄደ ያለው ፊልሚያ የአሃዳዊ አስተሳሰብ አቀንቃኞች በአንደኛ ጎራ የተሰለፉበት በሌላኛው ጎራ ደግሞ የራስን እድል በራስ በመወሰን የሚያምኑና ይህንኑ እውን ለማድረግ ሁለንተናዊ መስዋእትነት እየከፈሉ ባሉት ታጋዮችና ህዝቦች መካከል መሆኑን በውል ሊገነዘቡ ይገባል ብሏል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝቦች ከ31 ዓመታት በፊት ብሩህ ጉዞ በማብሰር ተጨባጭ ትሩፋቶች ያስገኘው ግንቦት 20 በዓልን ሲያከብሩ የራሳቸውን እድል በሪፊረንደም ለማረጋገጥ ከሚፋለሙት ሀይሎች ጋር ወግነው የድርሻቸውን እንዲወጡ የትግራይ መንግስት ጥሪ አቅርቧል፡፡