Home ዜና የትግራይ   መካነ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን  ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን  ግንኝነቱ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡

የትግራይ   መካነ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን  ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን  ግንኝነቱ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡

853

የኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸመና እየተፈጸመ ያለውን ዘግናኝ በደል እንድትቋወም እና ከተበደለው ህዝብ ጎን እንድትቆም ለቀረበላት ተደጋጋሚ ጥሪ በጎ ምላሽ ባለመስጠቷዋ በስሯዋ ሲተዳደር የቆየው የትግራይ የስራ ክፍል ግንኝነቱ ማቋረጡን አስታወቀ፡፡

የስራ ክፍሉ ግንኙነቱን ለሟቋረጥ የተገደደው ቤተ-ክርስቲያኒቷ የፋሽስት የአብይ ቡድን፣ የአምባገኑ የኢሳያስ ወታደሮች እና የተስፋፊው የአማራ ሃይሎች ተቀናጅተው በትግራይ ህዝብ ላይ እጅግ ሊናገሯዋቸው የሚከብዱ ዘግናኝ ግፎችና በደሎችን መፈጸም ከጀመሩ ከ500 ቀናት በላይ ቢያስቆጥርም ቤተ-ክርስቲያኒቷ በደሉን እንዲቆም ያሳማችው እና የወሰደችው እርምጃ ባለመኖሩ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የትግራይ የስራ ክፍል፣ ከቤተ-ክርስቲያኒቷ ጋር የነበረውን ተቋማዊ አስተዳደርና ግንኙነት ከመጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ እና የቤተ-ክርስቲያኒቷ ከፍተኛ መሪዎች እንደማይወክሏቸው ባወጣው የአቋም መግለጫ አረጋግጧል፡፡

በቤተ-ክርስቲያኒቷ የትግራይ የስራ ክፍል ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በስራ ክፍሉ በደረጃው ባሉት የእምነቱ ተከታዮች እና ማህበራት ሲያካሄደው የቆየውን ምክክርና በመጨረሻም በስራ ክፍሉ ፈጻሚ ቦርድ በኩል ውሳኔውን ተቀባይነት በማግኘቱ ነው ብሏል፡፡

ቤተ-ክርስቲያኒቷ ድምጽ ሌላቸው የትግራይ ህዝብ ድምጽ ትሆናቸዋለች፣ የጅምላ ግድያና ከነ ህይወታቸው እሳት ላይ በመጣድ መግደልን ጨምሮ በረሃብ፣ #በሽታ እና #ስደት ጉዳት እየደረሰበት ካለው የትግራይ ህዝብ ጎን ቆማ ከለላ ትሆናቿዋለች ቢባልም ተልእኳዋን በመሳት ምንም እንዳለለች ገልጿል፡፡ 

ጽድቁን ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንደሚባለው ሆነና ነገሩ፣ የቤተክርስትናይቷዋ የበላይ አመራሮች ይባስ ብለው የፋሽስቱ የአብይ ቡድን እና ሸሪኮቹ ባኖሩት ከበባና ክልከላ ምክንያት በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለውን በደል ለመግታት ታስቦ የወጣውን HR 6600 እና S3199 ረቂቅ ህጎችን በየሚድያው ቀርበው በመቃወም አሉታዊ ሚናቸውን እየተጫወቱ ይገኛሉ ብሏል የአቋም መግለጫው፡፡

በመሆኑም ይላል የትግራይ የስራ ክፍሉ ባአቋም መግለጫ ላይ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ እየሱስ እያሰማቸው ያለውን የተቋውሞ መግለጫዎች እጅግ የሚያሳፍርና እና እናት ሆኗ ድምጿዋን ለልጆቿዋ ማሳማት ባለማቿልዋ በየደረጃው በተደረጉ ጉባኤዎቻችን አረጋግጠናል ሲልም ነው ያስታወቀው፡፡

ቤተ-ክርስቲያኒቷ መንፈሳዊ ሃላፊነት እና አደራ የጎደለው ተግባር ፈጽማለች ያለው የአቋም መግለጫው፣ ለትግራይ ህዝብ ይቅርታ ጠይቃ እስካልተመለሰች ድረስ ከመጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ግንኝነቱን ሙሉ በሙሉ ማቋረጡን አስታወቋል፡፡

ከ2008 ዓ/ም እስከ 2013 ዓ/ም ድረስ የትግራይ ህዝብን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የተቀናጀ ሴራና ጥቃት እየተፈጸመ ቆይቷል፡፡ በኋላም የፋሽስት የአብይ ቡድን እና ግብረአበሮቹ ግልጽ የጆኖሳይድ ጦርነት በማወጅ ዘግናኝ ግፎችና ወንጀሎችን ተፈፅሞበታል ያለው መግለጫው ከተፈጸሙበት ግፎች መካከልም ጾታዊ ጥቃትን፣ ረሃብና የጅምላ ግድያን እንደጦር መሳሪያ መጠቀም ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እንዲሁም ኢትዮጵያ እንደ ሃገር መላው የትግራይ ህዝብን በመካድ ከካህን እስከ ጳጳሰ፣ ከህጻናት እስከ ከፍተኛ ምሁራን እና ከእምነት ተቋማት እስከ  የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ድረስ ልዩነት ሳይደረግባቸው እንዲወድሙ መደረጋቸውን የአቋም መግለጫው አስታውሳል፡፡

በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈጸሙትና እየተፈጸሙት ያሉትን እንዚህና መሰል ወንጀሎችን እንዲቆሙ በቤተክርስትያንቷዋ የትግራይ የስራ ክፍል ድርሻውን ሲወጣ መቆየቱን  በመግለጫው  አስታውቋል፡፡

አማረ ኢታይ