Home ዜና የትግራይ ምሁራን የሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ የ2021  አለም አቀፍ የእርሻ ሽልማት አሸናፊ   የእንኳን...

የትግራይ ምሁራን የሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ የ2021  አለም አቀፍ የእርሻ ሽልማት አሸናፊ   የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፉ፡፡

835

አለም አቀፍ የትግራይ ምሁራንና ባለሙያዎች ፕሮፌሰር ምትኩ የ2021 የእርሻ አለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው በተዘጋጀ የእውቅና ስነ-ስርአት የእንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላለፈ፡፡

ዓለም አቀፍ የትግራይ ምሁራን ማህበረ-ሰብ ቦርድ እና አባላት ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ ከዓለም አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኮንፌደረሽን የእርሻናተፈጥሮ ሀብት ሳይንስ ማህበር የተበረከተላቸውን ሽልማት ምክንያት በማድረግ የተሰማውን ደስታ ሲገልፅ ፕሮፌሰሩ ሽልማቱን የመካከለኛው ዘመን በሚመስል ከበባና ክልከላ ምክንያት በአካል ተገኝተው ለመቀበል አልቻሉም ብላል፡፡

ፋሽስት የአብይ ቡድንና ግብረ ግብረአበሮቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት ምክንያት ኑሮውን ከተመሰቃቀለበት  7 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ መካከል አንዱ ፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ ናቸው ለው የማህበረሰቡ መግለጫ ፡፡

በዚህም ሎሬት ፕሮፌሰር ምትኩን ጨምሮ በርካታ ምሁራን ለትግራይ፣ ለኢትዮፕያ፣ ለአፍሪካና ለተቀረው ዓለም  ሊያበረክቱት የሚገባን አስተዋጽኦ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን በትግራይ ህዝባዊ አገልግሎቶችን በመዝጋቱ ምክንያት የመስራት መብታቸውን መነፈጋቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

GSTS  በዚሁ መግለጫው  የመቐለ የኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ክፍል የቀድሞ ዲንና የቀዶ ጥገና ተባባሪ ፕሮፌሰር ደ/ር ፋሲካ አምደ ስላሴ በከበባውና ክልከላው ሳቢያ ተረጂ ለመሆን መብቃታቸው በማስታወስ USAID ለሰጣቸው የ100 ኪሎ ስንዴ አስር ኪሎ አተርና ሶስት ሊትር እርዳታ ማመስገናቸውን የሚገልፅ ጽኁፍ አስፍሯል፡፡

የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና ተባባሪ የቀዶ ጥገና ፕሮፌሰር  ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ በበኩላቸው አንድ ቀን እራት ይኖረኛል ብለው ለኢትዮጵያውያን የሙያ አጋሮቻቸቸው ያስተላለፉትን የምኞት መልእክት ያሰፈረው  መግለጫው የትግራ ፕሮፌሰሮችና ተመራማሪዎች እንዲሁም የባንክ አገልግሎት በመቋረጡ ከአንድ አአመት በላይ ያስቆጠሩትን ከ300 ሺህ በላይ የትግራይ መንግስት ሰራተኞች ባሁኑ ሰአት እያሳለፉት ያለውን የስቃይና መከራ ህይወት ገልጧል፡፡

ፋሽስት የአብይ ቡድንና ግብረአበሮቹ  በትግራይ ህዝብ ላይ ባወጁት የጀኖሳይድ ጦርነት አራት የአክሱም ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰሮችን ጨምሮ ብዙዎችነ ከህግ አግባብ ውጭ በሆነ ሁኔታ መገደላቸው ያስታወሰው መግለጫው  ከመገደላቸው በተጨማሪ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ አስተማሪና ተመራማሪ የነበሩት ፕሮፌሰር ማአረግ አማረ በማንታቸው ምክንያት መገደላቸው አስታውሷል፡፡

በዚሁ ሁሉ መከራ መሀል ሆነን ነው የፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለን አለም-አቀፍ የሎሬት ሽልማትን እያከበርን ያለነው ብሏል GSTS  

በዓይደር  ኮምፕረሄሲቭ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ የቀዶ ህክምና ተባባሪ ፕሮፌሰር ፋሲካ አምደስላሴ  አሜሪካ 100 ኪሎ ስንዴ፤ 10 ኪሎ አተርና ሶስት ሊትር ዘይት ስለሰጠችኝ አመስግናለሁ ሌላው በዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተባባሪ ፕሮፌሰርና ከፍተኛ ክሊኒካል ዳሬክተር  ክብሮም ገብረስላሴ አንድ ቀን እራት ይኖረኛል የሚል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ የለጠፉት ፅሁፍ በትግራይ ህዝብና ምሁራን ላይ ምን ያህል ችግር መንሰራፋቱን ያመለክታል ብሏል፡፡

ሌሎች በርካታ የትግራይ ተወላጅ ምሁን ምንም አበሳ ሳይነራቸው በማንነታቸው ምክንያት እስር ቤት ውስጥ እየማቀቁ ባሉበት ጊዜ የፕሮፌሰር ምትኩ ሀይለ የሽልማት ስነ ስርዓት በማክበር ላይ እንደሚገኙ መግለጫው ጠቅሰዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማራማሪዎችና አስተማሪዎችን ጨምሮ ከ300ሺህ በላይ የሚበልጡ የመንግስት ሰራተኞች ለ20 ወራት ያህል ያለ ምንም ደሞዝና ክፍያ መራራ ኑሮ እየገፉ እንደሚገኙ መግለጫው አመልክቷል፡፡

መብራህቱ ይባልህ