የትግራይ ሰራዊት ዋና ኣዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ / ወዲ ወረደ/ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሰቆጣ በኩል ወደ ትግራይ ሰብሮ ለመግባት ጦርነት መክፈቱን ኣስታወቀ፡፡
ወደ ኤርትራ የተዘዋወረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም በኣዳያቦና፣ ኣስገለ እና ራማ የመድፍ ድብደባ እያካሄደ ነው ለመመከትም በዝግጅት ላይ ነን፡፡
የኤርትራ ሰራዊትም በወረራው ተሳታፊ መሆኑን ታውቋል ብሏል ዋና ኣዛዡ፡፡
ዋና ኣዛዡ በመግለጫቸው የትግራይ ሰራዊት በቀጣይ ለህልውናቸው እና ለመብታቸው ከሚታገሉ የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር አንደሚተባበሩ ኣስታወቁ፡፡
የትግራይ ሰራዊት የውግያ ጥበብና ሰልት ብሎም የማደረግ ኣቅም ተገዶ በገባበት እና የተከፈተበትን ወረራ ለመከላከል ግዙፍ የጠላት ሃየል በመደምሰስ ኣያሌ ኪሳራ ማድረሱን ኣረጋግጧል ብሏል፡፡