Home ዜና የትግራይ ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ፍትሕ እንዲያገኙ የፀጥታው ምክር ቤት ጠየቀ፡፡

የትግራይ ሴቶች ፆታዊ ጥቃት ፍትሕ እንዲያገኙ የፀጥታው ምክር ቤት ጠየቀ፡፡

840

ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ፍትሕ እንዲያገኙ እና ወንጀለኞችም ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አስታወቀ።

በምክር ቤቱ የጾታዊ ጥቃት ልዩ ተወካይ ፕራሚላ ፓተን በትግራይ ሴቶች ላይ የተፈፀመውን ጨምሮ በተለያዩ አለማት በሚገኙ ሴቶች ላይ የተፈፀመው የፆታ ጥቃት ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ  ጊዜ  በፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች መዝገብ ላይ አስፍሯታል፡፡              

ፋሽስታውያን እና ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ ባካሄዱት የጀኖሳይድ ጦርነት ላይ በትግራይ ሴቶች ላይ የተፈፀመው አስነዋሪ ተግባር የአለም ማህበረ-ሰብ በፅኑ የኮነነው አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡

በትግራይ ሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃትን እንደ ጦር መሳሪያ የመጠቀም ወንጀል አለም ማውገዙን እና ድርጊቱን መኮነኑ አሁንም ቀጥሎበታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤትም ለኘጀመሪያ ግዜ በትግራይ ሴቶች እና በተለያዩ የአለም ሀገራት ሴቶች ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ፆታዊ ጥቃት በአጀንዳነት ተወያይቶበታል፡፡

የምክር ቤቱ የጾታዊ ጥቃት ልዩ ተወካይ ፕራሚላ ፓተን በፋሽስቱ ሰራዊት የአባገነኑ ኢሳያስ ቅጥረኛ ወታደሮች  የአማራ ተስፋፊ ሀይሎች በቅንጅት በትግራይ ሴቶች ላይ ፆታዊ ጥቃትን  እንደ ጦር መሳርያ ተጠቅመዋል ብለዋል፡፡

ስለሆነም በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን ከበባና ክልከላ መቀጠሉን ተከትሎ በተደፈሩ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተፅኖ መፍጠሩን  በመግለፅ የአለም  ማህበረ-ሰብ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ፕራሚላ ፓተን ለፀጥታው ምክር ቤት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕራሚላ ፓተን የችግሩን አስከፊነት በምሳሌ ሲያስረዱ 27 የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት ወደ መጠለያ ካምፕ በመውሰድ አንዲት ትግራወይቲ በአሰቃቂ  መልኩ እንደደፈሯት  አንስተዋል፤ በዚህም ለኤች አይቪ  ኤድስ በሽታ መጋለጧን ገልጸዋል፡፡

አክለውም #ሑመራ ይኖር በነበረ አንድ ወንድ ትግራዋይ ላይም የሰው ባህሪ በሌላቸው በአምባገነኑ የኢሳያስ ወታደሮች ግብረሰዶማዊ ጥቃት እንደፈፀሙበት በዚህ ምክንያት  ወጣቱ ህይወቱን ማጥፋቱ ፕራሚላ ፓተን ለጉባኤተኞቹ አብራርተዋል፡፡
ፕራሚላ ፓተን እንደገለፁት እንደዚህ አይነት ወንጀል የፈፀሙ አካላት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ መሰራት እንደሚገባ በመግለፅ የተደፈሩት እንስቶች የህግ ከለላ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ መፍትሄ ካገኘም የገፈቱ ቀማሽ የሆኑትን እና እየሆኑ ያሉት በትግራይ፣ ዩክሬን አፍጋኒስታ እና በማይናማርን የሚገኙ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች እምባቸው ይታበሳል ሲሉም አክለዋል፡፡

ፕላሚራ ፓተን በጉባኤው ከ18 በላይ ፆታዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው የአገራትን ዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ይህም በአለም ላይ ምን ያህል የሴቶች ፆታዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡ 

ድርጅቱ ትናንት ባካሄደው ጉባኤም ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ  ጊዜ  በፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች መዝገብ ላይ አስፍሯታል፡፡

ብርቱካን ጌታየ