በማንነታቸው ምክንያት በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ተወላጆችን የሚታጎሩባት እና የሚሰቃዩባት አዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ ሴት አትሌቶች በዓለም መድረክ ያስመዘገቡትን አንፀባራቂ ድል ምክንያት በማድረግ ደስታዋን ስትገልፅ ውላለች።
በስነ ስርዓቱ የተገኘችው እውቋ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ድል ላስመዘገቡት የትግራይ ተወላጅ ሴት አትሌቶች እንደወትሮው ያላትን ክብር በመግለፅ በትግራይ የተዘጉ መሰረታዊ የህዝብ አገልግለቶች እንዲከፈቱ ድምፅዋን አሰማች።