Home ዜና የትግራይ አርሶ አደሮች የእርሻ ግብአት ባለማግኘታቸው  የዘንድሮ የመኸር ምርት ዘመን እያለፈባቸው እንደሆነ...

የትግራይ አርሶ አደሮች የእርሻ ግብአት ባለማግኘታቸው  የዘንድሮ የመኸር ምርት ዘመን እያለፈባቸው እንደሆነ ተገለፀ፡፡

889

የትግራይ አርሶ አደር የእርሻ ግብአት እንዳያገኝ በፋሽስቱ ቡድን ሆን ተብሎ የተኖረው ክልከላ ረሃብ እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመበት መሆኑን መሳያ ነው ተብሏል፡፡

አርሶ አደር የተሻለ ምርት እንዲያገኝ የእርሻ ግብአት በተለይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ሊቀርበለት እንደሚገባ የሚታወቅ ሲሆን በያዝነው ክረምት ግን የትግራይ አርሶ አደር  ለዚሁ አልታደለም፡፡ እስካሁን የቀረበለት የእርሻ ግብአት የለም፡፡

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ ቆራሮና ታሕታይ አድያቦ ወረዳዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች የአፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር የመሳሰሉ መሰረታዊ የእርሻ ግብአቶች ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረጉና የምርት ዘመኑ እያለፈባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መሬታችን የአፈር ማዳበሪያ ለምዷል፣ ያለመዳበሪያ ደግሞ የሚታፈስ ምርት አይኖርም የሚሉት አርሶ አደሮቹ  በዚህ ክረምት ካላመረትን ቀጣይ አመት የከፋ የረሃብ አደጋ ያጋጥመናል የሚል ሰጋት አለን፣ በቀረችን ትንሽ ጊዜ ቢሆን የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ የእርሻ ግብአት እንዲያስገባልን እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የአዝርእትና ሰብል ጥበቃ ባለሙያ አቶአዱኛ ገብራይ በበኩላቸው ከጀኖሳይዳል ጦርነቱ በፊት በዞኑ 130 ሺህ ኩንታል መዳበሪያና በቂ ምርጥ ዘር በመጠቀም ከ240 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በማልማት ትርፍ ምርት ይገኝ እንደነበር አውስተዋል፡፡

በዚህ አመት አርሶ አደሩ ምንም አይነት የእርሻ ግብአት እንዳልቀረበለ የተናገሩት ባለሙያው ይሄ ደግሞ የፋሽስቱ ቡድን ሆን ብሎ  ረሃብ እንደጦር መሳሪያ እየተጠቀመበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሚመለከተው አካል ለአርሶ አደሩ ሊደርስለት ይገባል ሲሉም ጥሪያቸው አስተላልፈዋል፡፡

ወ/ሚካኤል ገ/መድህን