የዓለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ ከተለመደው አባባል ወጥቶ በፋሽስቶችና በተስፋፊው የአማራ ሊሂቃን ተጨባጭ እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ አሁን ነው ሲል የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡ተስፋፊው የአማራ ሃይል በፈፀመው ኢሰብአዊ ወንጀል ከተጠያቂነት ለማምለጥ የማስረጃ ደብዛ እንዲጠፋ እያደረገ ነው ብሏል ቢሮው፤የትግራይ መንግስት ውጭ ጉዳዮች ቢሮ የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች በትግራይ ጀኖሳይድ ሰለባ የሆኑትን ወገኖች አፅም የማርከስ ተግባር በሚል እርእስት በወጣው መግለጫ የአማራ ተስፋፊ ሃይል በትግራይ የጀኖሳይድ ሰለባ የሆኑትን ወገኖች አፅም ሆነ ብሎ በማስወገድ የማስረጃው ደብዛ እንዲጠፋ በማድረግና በማውደም የማርከስ ተግባር መጠመዱ አውግዟል፡፡
የትግራይ ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በታቀደው የጀኖሳይድ ፕሮጀክት ህልቅ መስፈርት በሌለው መረጃና ማስረጃ የተደራጀ መሆኑን ያመለከተው የትግራይ መንግስት የውጭ ጉዳዮች ቢሮ የፋሽስቱ አብይ ቡድንና የአምባገነኑ ኢሳያስና ሰራዊት ከተስፋፊው የአማራ ሃይል ጋር በማበር በትግራይ ህዝብ ላይ ዘግናኝ ግፎች መፈፀማቸውና በመፈፀም ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል፡፡እነዚህ የጀኖሳይድ ሃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ ጀኖሳይድ ወንጀል በመፈፀም፣ ሆነ ተብሎ የታቀደ በሴቶችና ልጃገረዶች በቡድን የተደራጀ ፆታዊ ጥቃት በማካሄድ፣ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል እንዲሁም ዘርን የማፅዳት ተግባር በማከናወን የትግራይን ኢኮኖሚ በማዳከም የማህበረ ባህላዊ ተቋማት በማውደም ርሃብን እንደ ጦር መሣርያ በመጠቀም እንዲሁም የመሠረተ ልማት አውታሮችን በማፈራረስ በርካታ ግፎች ፈፅመዋል በመፈፀም ላይም ይገኛሉ ብሏል፡፡
ትግራይ ለ8 ወራት በወራሪ ሃይሎች ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ግፎች በሚመለከታቸው ተቋማትና በሚድያ ተቋማት በአግባቡ ተሰንደው እንደሚገኙ ያመለከተው ቢሮው ሰኔ 2013 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ጠላቶች በጀግናው የትግራይ ሰራዊት ከምድረ ትግራይ ተጠራርገው አንዲወጡ መደረጋቸው አስታውሷል፡፡ የምዕራብ ትግራይን አካባቢ በሙሉ የሰሜን ምዕራብና ምስራቃዊ ትግራይ ደግሞ በከፊል አሁንም ጭካኔ በተሞላበት አኳሃን በጠላት ሃይል እንደሚገኙ ያመለከተው ቢሮውየአማራ ተስፋፊ ሃይሎች በምዕራብ ትግራይ አንዳች የትግራዋይ ምልክት የሆነን ነገር ደብዛውን ለማጥፋት ሁሉም አቅማቸውን የፈቀደው ከማድረግ እንዳልተቆጠቡ ያመለከተው ቢሮው በውጤቱም የምዕራብ ትግራይ ህዝብ ዋነኛ የገፈቱ ቀማሽ እንደሆነ አመላክቷል፡፡የተዛቡ ታሪካዊ ግንኙነቶች ይበልጥ እንዲባባሱ በማድረግ የተስፋፊው የአማራ ሊሂቃን ወደርየለሽ ናቸው ይላሉ መግለጫው ምዕራብ ትግራይን ጠቅልለው መያዛቸው አስታውቋል፡፡
የአምባገነኑ ኢሳያስ የጀኖሳይድ ሰራዊት ምዕራብ ትግራይን በሙሉ ሰሜን ምዕራብና ምሥራቃዊ ትግራይን በከፊል አሁንም ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ አመላክቷል መግለጫውይህ በሞራል የዘቀጠው ልሂቅ የሚያቀርበው የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ህጋዊ መሠረት የሌለው በመሆኑ ጥያቄውን በሕገ መንግስቱ እውቅና ያገኘውን የትግራይ የግዛት እንድነትን በሃይል የመያዝ አማራጭ በመውሰዱ በአካባቢው አዲሱ የህዝብ አሰፋፈር እየፈጠረ ነው ብሏልበአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት እንደተረጋገጠው በአካባቢው የዘር ማፅዳት ተግባር በማካሄድ የአማራን ማህበረ-ሰብ ወደ አካባቢው በማስፈር የመሬት ጥያቄውን ህጋዊነትን ለማላበስ እየጣረ ይገኛል ብሏል መግለጫው፡፡
ይህነኑ እኩይ ተግባራቸውን ለማሳካት ተስፋፊው የማራ ሃይል ወራሪው የአምባገነኑ የኢሳያስ ሠራዊት ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገበትና በፋሸስቱ የአብይ ቡድን ሙሉ ትብብር በማግኘት በምዕራብ ትግራይ ህዝብ ላይ ዘግናኝ ግፎች እየተፈፀመ እንደሆነ አመላክቷል፡፡ከአንድ ዓመት በፊት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት በኩል በምእራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት ተግባር መከናወኑ ይፋ ቢሆንም ይህንኑ እየተፈፀመ ያለው ወንጀል ጀኖሳየድ ተብሎ በስሙ አልተጠራም እርምጃም አልተወሰደም ብሏል ቢሮው፡፡ይህ በዘራፊው የአማራ ልሂቅ የተፈፀመው ኋላ ቀርና አረመኔያዊ ተግባር ከሁለት ሚልዮን በላይ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ህዝብን ማፈናቀሉንና ከ70 ሺ በላይ የትግራይ ተወላጆች ደግሞ ወደ ሱዳን ለስደት እንደዳረጋቸው አስታውቋል ቢሮው፡፡
ዓለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ ጀሮዳባ ልበስ በማለት ያሳየው ግድየለሽነትና ቸልተኝነት የፋሸስቱ የአብይ ቡድን የአምባገነኑ ኢሳየስ ተስፋፊውን የአማራ ሃይል በዚሁ አረመኔያዊ ተግባራቸውን እንዲቀጥሉበት ማደፋፈሩ ያትታል የቢሮው መግለጫ፡፡ በአለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ ግድ የለሽነትነ እርምጃ ያለመውሰድ የተነሳ የተደፋፈረውና በሚያካሂደው የጭካኔ ተግባር የሚደሰተው ተስፋፊው የአማራ ሃይል ህገ-ወጥነቱን ለአለም ማህበረ-ሰብ ለማሳየት የማይቆፍረው ጉድጔድ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ብሏል፡፡
በቁስል ላይ ጨው መጨመር እንዲሉ የፈፀማቸው አረመኔያዊና ኋላ-ቀር ዘግናኝ ግፎች አልበቃ ብሎት ተስፋፊው የአማራ ሃይል የጨፈጨፋቸውን የትግራይ ተወላጆች አፅምን ከጅምላ መቃብር በማውጣት የማራከስ ተግባር በመሰማራት ማስረጃ እንዲጠፋ እያደረገ ነው ብሏል፡፡ ተስፋፊው የአማራ ሃይል በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄደው ጭፍጨፋ የተፈፀሙ ግፎችን የሚያስረዱ ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ መኖራቸውን ያመለከተው የቢሮው መግለጫ በጅምላ መቃብሮች የሚገኙ አፅም ማንነትን በተመለከተ የተዛባ መረጃን በማስተላለፍ ላይ መጠመዱ አስረድቷል፡፡ተስፋፊው የአማራ ሃይል በትግራይ ህዝብ ላይ ያካሄደው ጭፍጨፋ ለመደበቅና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሙካራ እያደረገ መሆኑንም ያመለከተው ቢሮው ያስረዳል፡፡
ተስፋፊው የአማራ ሃይል የትግራይ ተወላጆችን በማጠልሸት የሃሰት ክስ እያቀረበ ዓለምን ለማታለል እየተጋ መሆኑን ያመለከተው ቢሮው የፈፀመው ወንጀል ሌሎችን በመውቀስ አካሄድ ብዙ ሊያራምደው አይችልም ብሏል፡፡የትግራይ መንግስት በትግራይ ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የተፈፀሙ ግፎች በዓለም አቀፍ ገለልተኛ አካል እንዲጣሩ ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱ የገለፀው ይህ መግለጫ ወራሪ ሃይሎች በትግራይ ሃይሎች ሰይጣናዊ ወንጀሎች እየተፈፀመ በማስመሰል ጨኩታቸውን ሲያሰሙ እንዳልቆዩ ሁሉ ወንጀሉ በገልልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ይታይ ሲባሉ አምርረው መቃወማቸውን አስረድቷል፡፡
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን እንዳይቋቋም ጥረት ማድረጋቸው ያመለከተው ቢሮው የትግራይ መንግስት ለኮሚሽኑ ሙሉ ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርግ ማስታወቁ አስታውሷል የቢሮው መግለጫ፤ ፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ተስፋፊው የአማራ ልሂቅ ካለምንም ሀፍረት ልበ-ወለዳዊ ትርክት ለመፍጠር የጨፈጨፋቸው የትግራይ ተወላጆች አፅምን ከመቃብር በማውጣት የማራከስ ተግባር መጠመዳቸው የገለፀው ቢሮው አለም አቀፉ ማህበረ-ሰብ በፋሸስቱ ዓብይ ቡድን በአምባገነኑ ኢሳያስና በዘራፊው የአማራ ተስፋፊ ሃይል እርምጃ የሚወሰዱበት ጊዜ አሁን መሆኑን አስገንዝቧል ቢሮው በመግለጫው፡፡