የትግራይ መንግስት በምህረት የለቀቃቸው ምርኩኞች ወደ ቀያቸው ለመመለስ ያሳለፈው ውሳኔ የትግራይ ህዝብ ሌሎች ህዝቦችን በክብር በሰብአዊነትና በመልካም ምግባር ከማስተናገድ የቆየ ልዩ ታሪኩ በመነሳት እንደሆነ የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
የዓለም አቀፍ ማህበረ-ሰብ በትግራዋይነታቸው ምክንያት በየእስር ቤቱ እየማቀቁ ያሉትን በአስር ሺዎች የሚቁጠሩ የትግራይ ተወላጆችን ከእስር እንዲለቅ በፋሽስቱ የአብይ ቡድን ላይ ጫና እንዲያደርግ ጠይቋል።