Home ወቅታዊ ጉዳይ የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅ/ቤት መግለጫ

የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅ/ቤት መግለጫ

724

በHumanraghtswotch & amnesty  በቅርቡ ይፋ የሆነው የጋራ ምርመራ ውጤት በምዕራብ ትግራይ ህዝብ ከተፈፀመው ወንጀል አንፃር ሲታይ በበቂ ደረጃ አልተሰነደም ሲል የትግራይ ውጭ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የትግራይ መንግስት Humanrightswotch & amnesty  የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች ከአምባገነኑ ኢሳያስ  ከፋሽስቱ የአብይ ቡድን ሙሉ ድጋፍና ትብብር በማግኘት  በምእራብ ትግራይ በትግራይ ተወላጆች ላይ የፈፀሙትና በመፈፀም ላይ ያሉትን የዘር ማፅዳትና በሰብአዊ ፍጡር ላይ ያነጣጠረ ወንጀል በማጋለጣቸው አድናቆቱን ገልፆ ሁለቱም የሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች በጋራ የደረሱበት የጥናት ግኝት የአለም አቀፍ ማህበረ-ሰቡን ማስደንገጡ አስታውቋል ፡፡

“ከምድረ ገፅ እናጠፋቸኋለን”በሚል አርእስት በቀረበው የታቋማቱ ሪፖርት የተካተቱ አሰቃቂና ወንጀሎች አለም አቀፍ የጦርነት ህግንና አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ህግን የሚፃረሩ ወንጀሎችን መሆናቸው የትግራይ የውጭ ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡

ይሁንና ይላል የትግራይ የውጭ ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ እነዚህ በጥልቀት የተካሄዱ የምርመራ ግኝቶች የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ለማሰብ እንኳ የሚከብድ ግፍ በትግራይ ህዝብ ላይ በመፈፀም በመሬት ላይ አዲስ የህዝብ አሰፋፈር ወይም ዲሞግራፊ ለመፍጠር መሰረት የሌለውን የመሬት የይገባኛል ጥያቄን ለማራመድና በሃይል የወረሩትን የትግራይ ህገመንግስታዊ ግዛት ህጋዊነትን ለማላበስ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ሁለቱም የሰብአዊ መብት ተማጓች ድርጅቶች በጋራ ያካሄዱት ምርመራ ምንም እንኳን ሰፊና ጠለቅ ያለ ኡነታዎችንና ማስረጃዎችን ያካተተ ቢሆንም በትግራይ ህዝብ ላይ መልሶ መላልሶ ከተፈፀመው ወንጀል  አንፃር የምርመራው ውጤት በእጅጉ ትንሹን  ነው የነካካው ብሏል፡፡

ወራሪ ሃይሎች ኡነተኛና አጠቃላይ ምርመራ ለማካሄድ  የሚደረገው እንቅስቃሴ ማደናቀፋቸው በግልጽ የሚታይ ቢሆንም  በትግራይ ህዝብ ላይ የወረደውን አረመኔያዊ ወንጀልና የግፍ መጠን በሪፖርቱ  በአግባቡ አልተሰነደም ብሏል፡፡

ወራሪ የአማራ ሃይሎችና የውጭ ደጋፊዎቻቸው  በምእራብ ትግራይ በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ እስከተፈቀደ ድረስ በኣለም አቀፍ እውቅና ያገኙትን የሰብአዊ መብቶችን  ከመቼውም ጊዜ በላይ  ያለምንም ጠያቂ መጣሳቸው ይቀጥሉበታል በሏል ቢሮው በመግለጫው፡፡

 ሆነ ተብሎ የተቀነባበሩና ስፋት ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በጄኖሳይዱ ጦርነት በሁሉም የእርከን ደረጃ ከተሳተፉ የወንጀሉ ፈጻሚ ተዋንያን ብዛት አንፃር ተጠያቂ ሊሆኑ የሚችሉትን አካለት ተጠያቂ የሚሆኑት ተአማኒና ገለልተኛ ምርመራ በማካሄድ እንደሆነ የትግራይ መንግስት ጠንካራ እምነት መሆኑን ቢሮው አስታውቋል፡፡

ተቀባይነት ያለውና ተአማኒ ምርመራ ለማካሄድ በሚመለከታቸው ህጋዊ ስልጣን ባላቸው ተቋማት የፎረንሲክ ማስረጃዎችን በተግባር ላይ በማዋል እንደሆንም አስታውቋል መግለጫው፡፡

የአለምአቀፍ ማህበረሰብ በቅርቡ የአማራ ተስፋፊ ሃይል ባለስልጣናት ከዚህ በፊት የጨፈጨፉዋቸውን የትግራይ ተወላጆች  አፅም ከመቃብር በማውጣት የማስረጃ አሻራና ምልክትን ደብዛ እንዲጠፋ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ምርመራውን በእጅጉ ከባድ እንደደሚያደርገው በመገንዘብ በጥብቅ እንዲያወግዘው ጥሪውን አቅርቧል፤ የትግራይ መንግስት፡፡

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት የአማራ ተስፋፊ ሃይሎች፣ ከፋሽስቱ የአብይ ቡድንና ከአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን ጋር በመሆን በምእራብ ትግራይ የፈጸሙት ወንጀል  የዘር ማፅዳት ወንጀል ብሎ ከሰየመው ከአንድ ዓመት በላይ ቢያሰቆጥርም ይህንኑ ተከትሎ እርምጃ አለመወሰዱ ቢሮው አስታውሷል፡፡

የተፈፀመው ወንጀል ጭካኔና ስፋት የአለም ማህበረሰብ ህሊናን የሚጎዳ ሆኖ ሳለ  ባጠቃላይ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ በምእራብ ትግራይ የጄኖሳይድ ወንጀል ስለ መፈፀሙ ለመወሰን  አንዳቃተው የትግራይ መንግስት  የውጭ ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ ያስረዳል፡፡

የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ ከነአካቲው ከጠፋ በኋላ  የተፈፀመው ወንጀል ጀኖሳይድ ነው የሚል ብያኔ የሚሰጠው ከሆነ ለህዝቡ ምንም የሚፈይደው ነገር የለውወም ያለው መግለጫው ፍጹም አይደገምም የሚለውን የአለምአቀፍ ማህበረሰብ ቃል ኪዳን  ትርጉም ሊኖረው የሚችለው በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ወንጀል በስሙ ሲጠራ ብቻ እንደሆነ የትግራይ መንግስት  የውጭ ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ አስገንዝቧል፡፡