Home ዜና የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካአል ውሎ በትግራይ ማዕከላዊ ዞን

የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካአል ውሎ በትግራይ ማዕከላዊ ዞን

የትግራይ #መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካአል ሰብአዊ እርዳታ ለማስገባት ታሰቦ የተደረገው ጊዜያዊ የግጭት ማቆም ስምምነ ጠላቶች ለማጭበርመበርና ጊዜ በመውሰድ ለተጨማሪ ቀውስ እንዳይጠቀሙበት መንግስት በትኩረትና በጥንቃቄ እንደሚሰራ ገለፁ። የትግራይ #ህዝብ ሰላም ፈላጊ ለነፃነትና ፍትህ የሚታገል ህዝብ ነው ያሉት የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን፣ በቀጣይ ህልውናችንን የሚያረጋግጠው በጅግናው ሰራዊታችን ነው ብለዋል። የትግራይ መንግስት ሰብአዊ እርዳታ በሚያስፈልገው ዓይነት፣ መጠንና ጊዜ ለትግራይ ህዝብ እንዲደርሰው የሚያስችል ሁኔታ ከተመቻቸ ከመጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበር ጊዜያዊ ግጭት የማቆም ስምምነት ማድረጉን ይታወቃል። ይህ #ስምምነት በትግራይ በተደረገው ከበባና ክልከላ በትግራይ ያጋጠመው የከፋ የሰብአዊ ቀውስ እንዲፈታ እድል ለመሰጠት ታሳቢ የተደረገ ስምምነት ነው። የትግራይ መንግስት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከትግራይ #ማዕከላዊ ዞን የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ህዝባዊ ውይይት አድርገዋል። የትግራይ #ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በህዝባዊ ውይይቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለሰብአዊነት ሲባል የተደረገው ጊዜያዊ የግጭት ማቆም ስምምነት በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ስምምነቱ በሂደት ተግባራዊ የሚሆነው አስፈላጊው #ሰብአዊ እርዳታ ተለይቶ ወደ ትግራይ በዓይነት በመጠንና በጊዜ የሚገባ ከሆነ ነው ብለዋል። የትግራይ ህዝብ ጠላቶች ውሳኔው ለማጭበርበርና ተጨማሪ ጊዜ ለመግዛትና ሰብአዊ #ቀውስ ለማባባስ እንዲቀጠሙበት አንፈቅድም ያሉት የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ስምምነቱ ክትትልና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገውና የትግራይ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራበት አረጋገጠዋል። የትግራይ ህዝብ ሰላም ፈላጊ ለነፃነትና ፍትህ የሚታገል ህዝብ ነው ያሉት የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የትግራይ ህዝብ በቀጣይ #ህልውናው የሚያረጋግጠው አንድነቱን አጠናክሮ ከሰራዊቱ ጋር ሲቆም ብቻ ነው ብለዋል።

1134