Home ዜና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው...

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች በሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው ተገለፀ።

1128

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሶማሊያ ውስጥ ሰፍረው የነበሩ ሁሉም ወታደሮቻቸው ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያሳለፉትን እርምጃን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቀልብሰው፣ የአሜሪካ የልዩ ተልዕኮ ኃይል አባላት በድጋሚ እንደሚያሰማሩ ተነግሯል።

ስለ ሰላም በመስበክ የሚታወቁት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ባሰሙት ንግግር ከአለም አቀፍ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ለበርካታ አስር ዓመታት የፀጥታና ደሕንነት እጦት እንዲሁም አሸባሪው የአል-ሸባብ ቡድን ሶማሊያን ከማናጋት አልፎ የአፍሪካ ቀንድ ስጋት ከሆነም ሰነባብቷል።

የበርካታ ሶማሊያውያን ደህንነት በሃገሪቱ ተሰማርተው በሚገኙ ከ19 ሺ በላይ የአፍሪካ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ሃይሎች ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ መመረጣቸውን ተከትሎ ከ500 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች  ወደ ሶማሊያ እንደሚላኩ  የአሜሪካ ሃገራዊ ደሕንነት ቃል አቀባይ ኤድሪን ዋትሰን ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡