Home Uncategorized የአሜሪካ ልኡካን የዘሄግ ውይይት 

የአሜሪካ ልኡካን የዘሄግ ውይይት 

848

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የግጭትና መረጋጋት ረዳት ሚኒስትር አኔ ዊትኮዊስኪ የሚመራ የልኡካን ቡድን ኔዘርላንድስ ዘሄግ ወደ ሚገኘው አለም አቀፍ የወንጀል ፍ/ቤት ማምራቱን ተገለፀ፡፡

ቡድኑ ከትናንት  ግንቦት 14 ጀምሮ እሰከ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም በኔዘርላንድስ ዘሄግ በሚኖረው ቆይታ ከአሜሪካ አጋርና ወዳጆች ጋር በትግራይ #ዩክሬን እና #በርማ እንዲሁም በሌሎች ሁከት በሚታዩባቸው አካባቢዎች ስለተፈፀሙ ግፎች አንስቶ ይወያያል ተብሏል፡፡

የአሜሪካው የልኡካን ቡድን ግፎች ሊፈፀሙባቸው የሚችሉ ሌሎች አካባቢዎች የመከላከልን እርምጃ ለመውሰድ የሚቻልባቸው ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

ሩስያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው ጦርነት የተፈፀሙትና በመፈፀም ላይ ያሉትን ግፎችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ወደ ህግ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ግምገማ የሚያደርግ ሲሆን ረዳት ሚኒስትሯ በኔዘርላንድስ ዘ ሄግ ቆይታቸው ከደች መንግስት አቻዎቻቸው በአውሮፓ ደህንነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የአሜሪካ #ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  አስታውቋል፡፡