Home ዜና የአሜሪካ መንግስት በትግራይ፣ አፋርና አማራ ለሚገኙ ተረጂዎች ወደ 313 ሚልዮን ዶላር የሚጠጋ...

የአሜሪካ መንግስት በትግራይ፣ አፋርና አማራ ለሚገኙ ተረጂዎች ወደ 313 ሚልዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

919

በትግራይ 90 ከመቶ የሚሆነውን ህዝብ እርዳታ ፈላጊ እንደሆነ USAID አመልክቷል፡፡               

ከ USAID የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አጋሮቹ ወደ ትግራይ በየብስ እርዳታን ለማጓጓዝ ከሚመለከታቸው አካለት ጋር እየተነጋገሩ ነው፡፡

USAID በአጋሮቹ አማካኝነት እስካሁን ድረስ እርዳታ ለሚሹ 105 ሺህ ሰዎች የሚበቃ የእርዳታ እህል አጓጉዘዋል፡፡

እርዳታው USAID በገንዘብ በሚደግፈውና የሰብአዊ አጋሮቹ አማካኝነት በአውሮፕላን የሚያቀርበውን ሰብአዊ እርዳታን የሚጠናክር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

በትግራይ ያለውን ሰብአዊ ቀውስን ለመፍታት ዘላቂ፣ ያለቅድመ ሁኔታና፣ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖር በየብስ ማጓጓዙን ብቸኛው አማራጭ መሆኑን USAID አመልክቷል፡፡

በትግራይ የኮሙኒኬሽን፣ ፋይናንስና ሌሎች መሰረታዊ ህዝባዊ  አገልግሎቶች እንዲጀምሩ መደረግ አለበት ብሏል USAID ፡፡

በእርዳታ ስንዴ ጥገኛ የሆነቸውንና የምግብ ዋስትናዋን ያላረጋገጠች #ኢትዮጵያ የ USAID ድጋፍ ተጠቃሚ ሆኗ ትቀጥላለለች  ብሏል፡፡