Home ዜና የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ብራድ ሼርማን   የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ...

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ብራድ ሼርማን   የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው  ጄኖሳይድ የመሆን አቅም ያለው ወንጀል በተመለከተ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት  የተሟላ ግንዛቤ እንዳላቸው  አመለከቱ፡፡

524

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል ብራድ ሼርማን   የፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ እያካሄደ ያለው  ጄኖሳይድ የመሆን አቅም ያለው ወንጀል በተመለከተ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት  የተሟላ ግንዛቤ እንዳላቸው  አመለከቱ፡፡

ስለሚወሰደው ግብረመለስም መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

ኮንግረስማን ብራድ ሸርማን በትዊተር መልእክታቸው የትግራይን ጄኖሳይድ በተመለከተ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር መወያየታቸው አመልክተው  ፕሬዚዳንት ባይደን በትግራይ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በተመለከተ የተሟላ ግንዛቤ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በትግራይ እየተካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት  ዘመቻን በተመለከተ ሊወሰድ ስለሚችለው ግበረመልስም እንዲሁ ሃሳቤን ለማዳመጥና ለመጋራት ፕሬዚዳንቱ ዝግጁ መሆናቸውና በተለይ ደግሞ የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት  ከትግራይና ከመላ ኢትዮጵያ ጠቅልሎ ስለሚወጣበት ሁኔታ መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡   

 ኮንግረስማን  ብራድ ሼርማን የፋሽስቱ ቡድንና አምባገነኑ ኢሳያስ በትግራይ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት  ያለውን ወንጀል ጄኖሳይድ  ነው በማለት ሽንጣቸውን ገትረው የሚከራከሩና ከትግራይ ህዝብ ጎን በመቆም አጋርነታቸውን እያሳዩ ያሉ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡