የአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን ሰራዊት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የሸራሮ ከተማን ለ23 ጊዜ በከባድ መሣሪያ መደብደቡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አረጋገጠ፤ በድብደባው የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ንብረት ወድሟል፡፡
Routers የዜና ምንጭ ከናይሮቢ ባሰራጨው ዜና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተባበሩት መንግስታት የለጋሽ ድርጅቶች ሰነዶችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው የአምባገነኑ የኢሳያስ ሠራዊት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ሸራሮን ቢያንስ ለ23 ጊዜ በከባድ መሣሪያ ድብድቧል፡፡
በዚሁ የአምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ሸራሮ ውስጥ የሚገኝ ተፈናቃዮች የተጠለሉበት ትምህርት ቤት ዒላማ ያደረገ ሲሆን የከባድ መሳሪያው ድብደባ የአንዲት የ14 ዓመት ህፃን ልጃገረድ ህይወት ቀጥፏል፣ በ18 ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፣ 12 መኖሪያ ቤቶች ደግሞ ጋይተዋል፡፡
የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት ቅዳሜና እሁድ በትግራይ ሃይሎች ላይ ትንኮሳ በማካሄድ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር የትግራይን መንግስት እንደምንጭ ጠቅሶ የዘገበው Routers የትግራይ ሃይሎች በአምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት ላይ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት እርምጃ አራት የአምባገነኑ ኢሳያስ ሰራዊት አዛዦች የተገደሉ ሲሆን 300 የአምባገነኑ ሰራዊት ከጥቅም ውጭ እንደሆኑ ዘገባው አመላክቷል።
የአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን ጦርነቱን ለማባበስ የሚያደርገው የተስፋ መቁረጥ እንቅስቃሴ አካል የሆነውን ይህንን ሙከራ ሸራሮን ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በከባድ መሣሪያ መደብደቡ በአምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት ሌላ እርምጃ እንድንወስድ እየገፋፋን ነው ሲሉ ማስታወቃቸው የትግራይ መንግስት ቃል አቀባይ የአቶ ጌታቸው ረዳ የትዊተር መልእክትን ጠቅሶ Routers ዘገቧል።
የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ ትናንት ባወጣው መግለጫ አምባገነኑ የኢሳያስ ሰራዊት ተጨማሪ የትግራይ መሬት ለመውረር ባደረገው ሙከራ የተከናነበውን ሽንፈት ተከትሎ ባለፈው ግንቦት 20 እና 21 2014 ዓ/ም በሸራሮ ከተማ ላይ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በማካሄድ በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው በነበሩ ሰላማውያን ሰዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ጉዳት ማድረሱን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ኩኖም ቀለሙ