Home Uncategorized የአብይ ቡድን ከተወገደ በኋላ የሃገሪቱ ህዝብ የራሱን ዕድን በህዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጥ መሰራት...

የአብይ ቡድን ከተወገደ በኋላ የሃገሪቱ ህዝብ የራሱን ዕድን በህዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጥ መሰራት እንዳለበት ተነገረ፡፡

624

በኢትዮጵያ ራስን በራስ ለመወሰን የሚታገሉ ሓይሎች ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ከተወገደ በኋላ የሃገሪቱ ህዝብ የራሱን ዕድን በህዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጥ ሲደረግ መሆኑን የሕግ ምሁርና #ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ፀጋዬ አራርሳ ገለፁ፡፡

ደ/ር ፀጋዬ ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ከተወገደ በኋላም በኢትዮጵያ ራስን በራስ ለመወሰን የሚታገሉ ሀይሎች መካከል አጋርነትን ለማጎልበት እና አብረው በሰላም ተማምነው ለመኖር የሚያስችላቸውን ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የደረሰው አስከፊ ሰብአዊ ቀውስ እና እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመኮነን በጋራ ድምፅ ማሰማት ይገባል ሲሉ የሕግ ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ፀጋየ አራርሳ ተናገሩ፡፡

ዶ/ር ፀጋየ የብሔሮች አጋርነትና የወደፊት ዕድላቸው በኢትዮጵያ በሚለው የመወያያ ሃሳብ ከትግራይ ሚድያ ሃውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ በፋሽስቱ ቡድን እና ግብረአበሮቻቸው በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የተቃጣው አደጋ ሰይፍ የማንሳቱ ጉዳይ የማይቀር በመሆኑ አንድ የሆነ የተባበረ ክንድ ማደራጀት ይገባል ብለዋል፡፡

ራሴን በራሴ አስተዳደራለሁ፤ ህዝብ ለሰጠኝ ስልጣን በህዝብ ድምፅ ብቻ ነው የማድሰው ላለው አካል የመናገር መብት ከመንጠቅ ጀምሮ እስከ የፌደራል ስርዓቱ ያጎናፀፈውን መብት ማሳጣት ደረጃ ተሂዷል፡፡ ሌሎች ጥያቄ ያላቸው ራስን በራስ ለመወሰን የሚታገሉ ሓይሎች ይበልጥ ያነሳሳል በማለትም በትግራይ ህዝብ ላይ የጀኖሳይድ ወንጀል ተፈፅሞበታል ያሉት ዶ/ር ፀጋየ አራርሳ የሃገሪቱ ህዝቦች በቀጣይ በጋራ ለመኖር ለመወሰን ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ከተወገደ በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱን ዕድን በህዝበ ውሳኔ እንዲያረጋግጥ ሲደረግ ነው ብለዋል፡፡

በህዝቦች መካከል ወንድሟሟችነት እንዲጎለብት፤ እውነተኛ አንድ  የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማ/ሰብ እንዲፈጠር የማድረግ ሃላፊነቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት ስራ ነበር ያሉት ዶ/ር ፀጋየ አራርሳ ይሁን እንጂ ምክር ቤቱ በሃገሪቱ ህዝቦች ላይ የጀኖሳይድ ጦርነት የሚያውጅ የፋሽስት ቡድን እጅ ላይ ወድቋል ሲሉ አክለዋል፡፡

ህዝቦች የራሳቸውን እድል የመወሰንና የመፈፀም አቅም እንዲመልሱ ማስቻል አስፈላጊ ነው ያሉት ደ/ር ፀጋየ ለዚህም ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ማስወገድና ከተወገደ ብኋላም በኢ/ያ ራስን በራስ ለመወሰን የሚታገሉ ሓይሎች መካከል አጋርነትን ለማጎልበት እና አብረው በሰላም ተማምነው ለመኖር የሚያስችላቸውን ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

ባለፉት 4 አመታት በሃገሪቱ የማሕበረሰብ ግጭቶች ተባብሰው እንዲቀጣጠሉ የፋሽስቱ ቡድን ሲቀሰቅስ ነበር ያሉት ዶ/ር ፀጋየ እንደ ውጤትም ማሕበረሰባዊ ጦረኝነት እንዲያይል ምክንያት ሆኗል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ስባጋድስ በላይ