Home ዜና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የዓለም ባንክ ያፀደቀውን የ300 ሚሊዮን ዶላር ጊዜው እንዳልሆነ አስገንዝቧል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን የዓለም ባንክ ያፀደቀውን የ300 ሚሊዮን ዶላር ጊዜው እንዳልሆነ አስገንዝቧል፡፡

866

የዓለም ባንክ   በግጭት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች  ያፀደቀውን የ300 ሚሊዮን ዶላር  የፋሽስቱ የአብይ ቡድን    ለጦር መሳርያ መግዝያ ሊያውለው እንደሚችል ተዘገበ፡፡ 

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን  በበኩሉ በትግራይ ጦርነቱ ባልቆመበት በአሁኑ ሰዓት ለመልሶ መቋቋም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ  አሁን ጊዜው እንዳልሆነ አስገንዝቧል፡፡                                                                                    

ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ   በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰቱ የእርስ በርስ  ጦርነቶች እና ግጭቶች የበርካቶችን ህይወት  ቀጥፏል፤ ሰብዓዊ ቀውሶች እንዲባባሱ፤ የግልና የህዝብ ተቋሟት እንዲወድሙ  አድርጓል፡፡

በተለይ  ፋሽስቱ የአብይ  ቡድን በትግራይ የጀኖሳድ ጦርነት ካወጀበት ጊዜ ጀምሮ   በሚልዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችን እንዲፈናቀሉ እና በትግራይ ሴቶች ላይ ፆታዊና ወሲባዊ  ጥቃቶች  በመፈፀም  ታዳጊዎች እና  ህፃናት ላይ አካላዊና   ስነልቦናዊ ጫና በመፈፀም አረመኔያዊ ግፍ አካሂዷል፡፡

 የዓለም ባንክ  በትግራይ ህዝብ ላይ በተከፈተው ጄኖሳይድ ጦርነት ምክንያት የተጎዱ ከ5 ነጥብ ሁለት ሚልን የትግራይን ህዝብ ጨምሮ ሌሎች ክልሎችን መልሶ ማቋቋሚያ በሚል ምክንያት የ300 ሚልዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍን  ማጽደቁ  ታውቋል፡፡   

በጦርነቱ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ፍላጎት በአስቸኳይ ለሟሟላት በትምህርት፣ በጤና፣ በውሃ እና በንጽህና  ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እንደሆነም ዲቪኤክስ የተሰኘ ድረ ገፅ ዘግቧል ።

የአለም ባንክ ድጋፉን የሚውለው በቀጥታ በጦርነቱ ለተጎዱ ክልሎች “ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ግለሰቦች በአካላዊ እና በአእምሯዊ ጤንነታቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ነው ቢልም  የተለያዩ የአለም አቀፍ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ከወዲሁ ያላቸውን ሰጋት እየገለፁ ይገኛሉ ፡፡

በትግራይ ከበባው እና ክልከላው ተጠናክሮ መቀጠሉን እና ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ለሰላም ሂደቱ ተባባሪ ከመሆን ይልቅ እንቅፋት በሆነበት በአሁኑ ጊዜ  ዐለም ባንክ  ይህንኑ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ  መወሰኑ   በርካታ ተንታኞች  በአሉታዊ ጎን እንዲመለከቱት ሆኗል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን  ቃል አቀባይ አለም ባንክ ገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑ ጊዜው አሁን እንዳልሆነ አመልክተዋል፡፡

 በኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ተንታኙ  የኢንተርናሽናል ክራይሲስ ጉሩፕ  ባልደረባ ዊልም ዴቪሰን በበኩሉ  ፋሽስቱ የአብይ ቡድን  በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ጦር መሳሪያ መግዥያ አጥቶ በመቆየቱ አሁን የተገኘውን ድጋፍ ለዛ ግብአት ሊያውለው እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፡፡