Home ዜና የአፍሪካውያን የሰላም ተምሳሌት ሆና ለሶስት አስርት ዓመታት የዘለቀችው ኢትዮጵያ  አሁን ላይ የኢሳያስ...

የአፍሪካውያን የሰላም ተምሳሌት ሆና ለሶስት አስርት ዓመታት የዘለቀችው ኢትዮጵያ  አሁን ላይ የኢሳያስ  መፈንጫ መሆኗተነገረ፡፡

1055

ባለፉት 27 አመታት ኢትዮጵያ ውጤታማ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በመተግበር እና ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በማከናወን፤ ውስጣዊ የሀገር ደህንነት እና ሰላም ከማረጋገጥ አልፋ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናም አስተማማኝ ሰላም እና ፀጥታ እንዲሰፍን ጉልህ ሚና ተጫውታለች፡፡

ኢጋድ እና አፍሪካ ህብረትን የመሰሉ አህጉራዊ ተቋማትን በማጠናከር እንዲሁም አለም-አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ልእልናዋን በመጎናፀፍ እንደ አምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ ያሉ አፍራሽ እና አተራማሽ ሚናን የሚጫወቱ አካላትን በአፍሪካ ቀንድ ቦታ እንዳይኖራቸው ማድረግ ችላ እንደነበር የፖለቲካ ምሁራን  ይናገራሉ፡፡ 

ይሁንና ከአራት አመታት ወዲህ የፋሽስቱ አብይ አሕመድ ቡድን በተከተለው ደካማ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የአምባገነኑ ኢሳያስ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ በቀጥታ እጁን እንዲያስገባ እና እንዳሻው እንዲፈተፍት እድል ሰጥቶታል፡፡

በጠንካራ ዲፕሎማሲ እና ውጤታማ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የምትታወቀው እና የሰላም ተምሳሌት የነበረች ሀገር በአሁኑ ወቅት የአምባገኑ ኢሳያስ የጥፋት መዳፎች ላይ ወድቃ በራሷ መቆም አቅቷት ስርዓት አልበኝነት ነግሶ በጎበዝ አለቃ የምትበጠበጥ በለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት የምትታመስ ሃገር ሆናለች ፡፡

የዚህ ሁሉ ምክንያትም የፋሽስቱ አብይ አሕመድ ቡድንና የአምበገነኑ ኢሳያስ ያልተቀደሰ ጋብቻ ውጤት መሆኑ ምሁራኑ ይገልፃሉ፡፡

የአፍሪካውያን የሰላም ተምሳሌት ሆና ለሶስት አስርት ዓመታት የዘለቀችው ኢትዮጵያ  የአምባገነኑ ኢሳያስ ቡድን መፈንጫ በመሆን ቀጠናዊ ሚናዋን ይቅርና  ለራሷም መሆን አቅቷት ሰላምዋ ተናግቶ፣ ኢኮኖሚዋ ላሽቆ፣ ዜጎቿ በማፈናቀል ከዓለም በአንደኝነት ደረጃ ተሰልፋ፣ የጦር ወንጀል እና የጀኖሳይድ ወንጀሎች የሚፈፀሙባት በመፈራረስ ጫፍ ላይ የምትገኝ ሃገር አድርጓታል፡፡