Home ዜና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች ታስረው የሚገኙ የአመራር ኣባላቱ በአፋጣኝ ከእስር...

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች ታስረው የሚገኙ የአመራር ኣባላቱ በአፋጣኝ ከእስር እንዲፈቱ ጠየቀ፡፡

986
0

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች ክስ ሳይመሰረትባቸው ታስረው የሚገኙ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር በተለያዩ ፖሊስ መምሪያዎች አባላትም አሳማኝ ማስረጃ ካልተገኘባቸው ሊፈቱ እንደሚገባና የተራዘመ ቅድመ ክስ እስር ሰዎች በፍትህ ኣስተዳደር ላይ ያላቸውን እምነት ያጠፋል ሲልም BBC በዘገባው አስፍሯል፡፡

ስድስት የፓርቲው አባላት ማለትም አቶ ሚካኤል ጎበና፣ አቶ ኬኔሳ አያና፣ ዶ/ር ገዳ ዋቂጅራ፣ አቶ ዳዊት እብደታ፣ አቶ ለሚ ቤኛ፣ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ገዳ ገቢሳ በቡራዮ ፖሊስ መምርያ የታሰሩ  ኮሎኔል ገመቹ አያና በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ማዕከል አቶ አብዲ ረጋሳ ገላን በሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ልዩ ፖሊስ #ካምፕ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙም BBC በዘገባው ኣትቷል፡፡

ሌላኛው የፓርቲው አባል አቶ በርጌሳ በእስር ላይ እያሉ ባጋጠማቸው ህመም በፖሊስ ዋስትና ተፈቅዶላቸው በህክምና ላይ እንደነበሩም አክሏል፡፡

ኣባላቱ #ፍርድቤት በዋስትና እንዲለቀቁ የፈቀደላቸው የክስ መዝገቦቻቸው ተዘግተው በፍርድ ቤት ውሳኔ በነፃ የተሰናበቱ፤ ምንም ኣይነት ክስ ያልተመሰረተባቸው መሆኑን በማረጋገጥ የምርመራ መዝገባቸው የተዘጋ ነው ብሏል BBC በዘገባው፡፡

በእስር ላይ የሚገኙት እነዚህ የኦነግ ኣመራር አባላት ከወራት እስከ ሁለት ዓመታት ለሚጠጋ ግዜ በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወሩ ህግን ባልተከተለ መልኩ የታሰሩ የተወሰኑትም በእስር ቆይታቸው ተገቢ ባልሆነ መልኩ የተያዙ፣ ድብደባ የተፈፀመባቸውና የአካል ጉዳቶችና ሌሎች የጤና እክል ያጋጠማቸው መሆኑን በዘገባው ተገልፃል፡፡

እስረኞቹ በተያዙበት  በፖሊስ ምረመራ ወቅትና በእስር ቤት ቆይታቸው ድብደባ ሲፈፀምባቸው እንደነበር መናገራቸውም BBC በዘገባው ኣስቀምጣል፡፡

ከነዚህ እስረኞች መካከል ስማቸው ያልተጠቀሰ እሰረኛ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር በአዋሽ መልካሳ ጊዚያዊ እስር ቤት ውስጥ በተፈፀመባቸው ድብደባ ጭንቅላታቸው ላይ እንደተፈነከቱና እግራቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልፃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በእስር ቦታ መጨናነቅ፣ በንፅህና ጉድለት፣ በምግብእጥረት፣ በህክምና እጦት ምክንያት ለህመም መጋለጣቸውን ለኣካል ጉዳት መዳረጋቸውን BBC በዘገባው ገልፃል፡፡

የኦነግ ፓርቲ ኣመራር አባላቱ  ለረዥም ግዜ ከህግ አግባብ ውጪ ታስረው የሚገኙ በመሆኑ በአፋጣኝ ከእስር ሊለቀቁ እንደሚገባና ለደረሰባቸው ጉዳት ሊካሱ የሚገባ ሲሆን በተጨማሪም የፍርድ ቤትና የዓቃቤ ህግ ውሳኔዎች በተደጋጋሚ እየተጣሱ እስረኞቹ ከህግ ውጭ ለተራዘመ እስር መዳረጋቸው ስልጣንን ያለ ኣግባብ መጠቀም ስለሆነ  ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድ አንደሚገባም በዘገባው ሰፍሯል፡፡

እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ #ምርጫ ቦርድ የግንባሩ ሊቀ-መንበር  ኣቶ ዳወድ ኢብሳ ለረዥም ግዜ በቤታቸው ውስጥ በቁም እስር ላይ መሆናቸው በመግለፅ ያሉበት ሁኔታ እንዲስተካከል የፀጥታ ኣካላት ጠይቆ ሊቀ-መንበሩ የመንቀሳቀስ መብታቸው እንዲከበር መደረጉ BBC በዘገባው በማውሳት ፅሁፉን ቋጭቷል፡፡

መአዛ መኮነን

Previous articleበጀግናው የትግራይ ሰራዊት በጦር ግንባር የተማረኩ ከ4200  በላይ የፋሽስቱ አብይ ቡድን የጦር ምርኮኞች በምህረት ወደ ቀያቸው ተሸኙ።
Next articleዘንድሮ የሚከበረዉን የንቦች ቀን በትግራይ ቀኑን ታስቦ እንዲዉል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተገለፀ፡፡