ፋሽስት የአብይ ቡድን ከተባባሪዎቹ ጋር በመሆን በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍ በአግባቡ በመገንዘብ የካናዳ መንግስት በፋሽስት የአብይ ቡድን ላይ ማእቀብ እንዲጥል አንድ የካናዳ ምክር ቤት አባል ጠየቁ፡፡
የምክር ቤቱ አባል አሌክስ ቡርንዴል ድካቤ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር በተገኙበት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተገኝተው እንዳሉት ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመው ዘግናኝ ግፍ የዓለም ማህበረ-ሰብ በሚገባ ሊገነዘበው ይገባል፡፡
አሌክስ ቡርንዴል ድካቤ የካናዳ የምክር ቤት አባል ናቸው፤ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስቴር በተገኙበት የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ፋሽስቱ የአብይ ቡድን ከተባባሪዎቹ ጋር በመሆን በትግራይ ህዝብ ላይ ዘር የማፅዳት ዘመቻ ጨምሮ የተለያዩ ግፎች እየተፈፀመ ነው ብለዋል፡፡
በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመውን ግፍ በአግባቡ በመገንዘብ የካናዳ መንግስት በፋሽስት የአብይ ቡድን ላይ ማእቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል።
አሌክስ ቡርንዴል ድካቤ እንዳሉት ፋሽስቱ ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመው ዘግናኝ ግፍ የዓለም ማህበረ-ሰብ በሚገባ ሊገነዘበው እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተውበታል፡፡
የዓለም ማህበረ-ሰብና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራት የሚገባቸውን ስራ ባለመስራታቸውና ያሳስበናል ከማለት በዘለለ ተጨባጭ እርምጃ አልወሰዱም ያሉት የምክር ቤቱ አባል አስቸኳይ እርዳታ ለሚፈልገው ከ6.5 ሚሊዮን በላይ የትግራይ ህዝብ ላይ በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ለታሪክ የሚቀር አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀሙ ነው ብለዋል፡፡
በትግራይ ህዝብ ላይ ዘር የማፅዳት ዘመቻ እየተፈፀመ ነው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ተጎድቷል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ እናቶችም ወሲባዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ይህም ማህፃናቸው ድጋሜ ህፃን እንዳያፈራ ተደርጓል፡፡ህፃናትም በፋሽስቱ ወታደሮች ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ ፋሽስቱ በከፈተው ጦርነት ምክንያት በሀገሪቱ ላይ ችግር ተደቅነዋል፡፡ የምስራቅ አፍሪካ አገራትም አለመረጋጋት በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመው ዘር የማፅዳት ወንጀልን ጨምሮ በትግራይ እናቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃትና ሌሎች ከባድ የሚባሉ የፀረ ሰብአዊነት ወንጀሎች ተፈፅሟል ያሉት የፓርላማ አባሉ ፋሽስቶችና ወራሪዎች አሁንም በትግራይ ህዝብ ላይ ከበባና ክልከላ በማበጀት ሌላ መልክ ያለው የእልቂት ወንጀል እየፈፀሙ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በካናዳ የሚገኙ ዲያስፖራ የትግራይ ተወላጆች ለሁለት ዓመታት ያህል የህዝባቸውን ሰቆቃና ስቃይ እንዲያበቃ ሳይታክቱ በመስራት የትግራይ ህዝብ ጉዳይ በካናዳ መንግስት ተገቢ ምላሽ እንዲሰጠው የምክር ቤት አባሉ ጠይቀዋል፡፡
በትግራይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ዲያስፖራዎች ለሁለት ዓመታት ያህል የትግራይ ህዝብ ጉዳይ በካናዳ መንግስት ትኩረት እንዲሰጠውና በተደጋጋሚ ጠይቋል፡፡ በፋሽስት የአብይ ቡድን ላይ ማእቀብ እንዲጣል የጠየቁት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
የካናዳ የፓርላማ አባል አሌክስ ቡርንዴል ድካቤ የፋሽስቱ ቡድን እና ተባባሪዎቹ በትግራይ ህዝብ ላይ ለፈፀሙት ጀኖሳየድ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና የትግራይ ህዝብም ፍትህ እንዲሰጠው በመጠየቅ በወንጀለኞች ላይ ማእቀብ እንዲጣልና ለፈፀሙት ወንጀል የሚመጥን ፍርድ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል፡፡
መብራህቱ ይባልህ