—-
ህገ-መንግስቱን የሚቃረን ክላስተሪንግ የሚል አዲስ የክልል አደረጃጀትም ተቃውሞ ገጥሞታል፤ የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ እና የወላይታ ህዘብ ዲሞክራስያዊ ግንባር ባወጡት መግለጫ የወላይታ ህዝብ በክልል ተደራጅቶ ራሱን በራሱን የማሰተዳደር መብቱን ተነግፎ ከሌሎች አጎራባች ህዝቦች ጋር እንዲደራጅ ተብሎ መወሰኑ ኢ-ህገ-መንግስታዊ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
ህዝቡ በራሱ ብቻውን በክልል መደራጀት ባይፈልግ እንካን የመጨረሻውን ውሳኔ መግለፅ የነበረበት በህዝበ ውሳኔ በመሆኑ በፋሽስቱ የአብይ ቡድን አስቀድሞ የተወሰነው ኢ-ህገ-መንግስታዊ ውሳኔ ተቀባይነት የለውም ብለዋል ፓርቲዎቹ ፡፡
ኢ-ህገ-መንግስታዊ ውሳኔውን የወሰነው የዞኑ ምክርቤት የስልጣን ጊዜው ያበቃ በመሆኑ በእንደዚህ አይነት የህዝብ ህልውና ሊፈታትኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ሊወስን የማይችል ተቋም በመሆኑ ውሳኔው ተቀባይነት የለውም ብለዋል፡፡
የወላይታን ህዝብ መጻኢ እድልብሩህ እንዲሆን የሚታገሉትን የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ እና የወላይታ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ግንባር እንዲሁም ሌሎች የሲቪክ ማህበራትን ያላሳተፈ አግላይ እና ጠቅላይ ውሳኔ እንደማይቀበሉት ፓርቲዎቹ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል፡፡
ክላስተር የሚባለው አደረጃጀት ከሀገሪቱ ህገ-መንግስትጋር የሚቃረን እና ለመተግበርም እጅግ አስቸጋሪ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ ውሳኔው በህገ መንግስቱ ላይ ክላስተር የሚል አደረጃጀት ስለሌለ እና የወላይታ ህዝብ ያልጠየቀው አደረጃጀት በመሆኑ ውሳኔው ተቀባይነት እንደሌለው አመልክተዋል የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ፡፡
ውሳኔው የህዝባችን ህልውና ሊያጠፋ ያለመ ሴራ ነው ያሉት የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ እና የወላይታ ህዝብ ዲሞክራስያዊ ግንባር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የወላይታ ህዝብ መብት እንዲረጋገጥ የወላይታ ቢሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሚል አማራጭ ያካተተ ህዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ የሚጠይቅ እና ሌሎች በለ ስምንት ነጥብ የአቋም መግለጫ እውጥተዋል ፡፡
በተመሳሳይ ዜና የፋሽስቱ ቡድን አዲስ ክላስተሪንግ የሚል አደረጃጀት ተከትሎ የጉራጌን ክልል የመሆን ጥያቄን ለማዳፈን በዞኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አካላት ላይ ጫና እየተደረገ መሆኑን እና የጉራጌ ምክር ቤት አባላትም በስብሰባ አለመሳተፋቸው ተገልጿል፡፡ የቀረበውን የፋሽስቱ ቡደን ሀሳብ ምክር ቤቱ እንደማይደግፍ የተረዳው የፋሽስቱ ቡድን በዞኑ ወልቂጤ ከተማ ላይ ከፍተኛ የፀጥታ ህይል ማሰማራቱን ታውቋል ፡፡
ውሳኔው ከብሄረሰቡ ተወላጆች ጠንከር ያለ ተቋውሞ ቢገጥመውም ይህ ክላስተር የተባለው አዲስ አደረጃጀት በጉራጌ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አለ ማግኘቱን ለOMN አስተያየታቸውን የሰጡ የጉራጌ ተወላጆች ይናገራሉ፡፡
በህገ-መንግስቱ መሰረት ጉራጌ የህዝብ ውሳኔ እንዲያካሄድ ለክልሉ ምክርቤት ከበቂ ማብራሪያ ያቀረበ ቢሆንም ክልሉ ምላሽ ባለመስጠቱ እና አሁን ላይ በፋሽስቱ የአብይ ቡድን የቀረበውን ክላስተሪንግ የሚል የአደረጃጀት ሀሳብ የጉራጌ ህዝብ አይቀበለውም የሚሉት አስትያየት ሰጪዎቹ ህገ መንግስታዊ የክልልነት ጥያቄ እንዲከበርላቸው አቋም መያዛቸውም ይናገራሉ፡፡
የፋሽስቱ ቡድን የህዝቡን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው የክላስተር አደረጃጀት በሚል የጉራጌን ህዝብ ያለ ፍላጎቱ ከሌሎች አከባቢዎች ጋራ እንዲደራጅ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ስብሰባ እንዳይጠራ ማድረጋቸውን ተከትሎ በአከባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የደህንነት እና የስለላ ቡድኖች እንዲሰማሩ መደረጉንም ከOMN ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ፡፡
በዋናነት ይሄን የህዝብ ውሳኔ ጥያቄ እንዳይመለስ እያደረገ ያለው የፋሽስቱ ቡድን ተላላኪ ሬድዋን ሑሴን ነው በማለት የጉራጌ ህዝብ ግን የክልልነት ጥያቄውን አጠናክሮ ይቀጥልበታል ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡
መአዲ ሀይለ