የዓለም ምግብ ፕሮግራም WFP ምንም እንኳን ሰብአዊ እርዳታ እያቀረበ ቢሆንም በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ምክንያት ለጋሽ ድርጅቶች ለሌሎች አካባቢዎች የሚደርጉትን የገንዘብ ድጋፍ እያሽቆለቆለ እንዲመጣ ምክንያት መሆኑን Globnews.net ዘገባ ያስረዳል፡፡
አብዛኛውን ትኩረትና የገንዘብ ድጋፍ ዩክሬን ለመርዳት እየዋለ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው ይህም ተገቢና መሆን ያለበትእንደሆነ አሰረድቷል ምክንያቱም በዩክሬን እየታየ ያለውን ቀውስ ጭምር አሳሳቢ በመሆኑ ነው ይላል፡፡
የአለም ምግብ ፕሮግራም WFP 70 ከመቶ የሚሆነውን ስንዴ ከዩክሬንና ከሩስያ በማስመጣት ለተረጂዎች የምግብ እርዳታ ሲቀርብ መቆየቱ ያመለከተው ዘገባው አሁን ግን የእህሉ ምንጭና የገንዘብ ድጋፉ አየደረቀ መምጣቱን አመልክቷል፡፡
የችግሩን አሳሳቢነትን በመገንዘብ ድርጅቱ ለተረጂዎች የሚያቀርበውን የእህል እርዳታ በተመለከተ በሚቀጥሉት ወራት አንዳንድ ለውጦች እንደሚደርግ አስታውቋል፡፡
የአለም ምግብ ፕሮግራም WFP ለእርዳታ የሚውልን በስንዴ ላይ ያለውን ጥገኝነትን በመቀነስ ከስንዴ ውጭ ባለ እህልና ጥራጠሬ ላይ እንደሚያተኩር ይሄው የግሎብ ኒውስ ዶት ኔት ዘገባ ያስረዳል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ያለውን ጦርነት እዲሁም የተከሰተው ድርቅ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ ቀውስ መባበስና በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሆኗል ብላል ዘገባው፡፡ በትግራይ #ጀኖሳይዱ ጦርነት በገፍ መፈናቀልን ያስከተለ ክስተት ተፈጥሯል ያለው ዘገባው በትግራይና በተቀረው የኢትዮጵያ ያለውን የረሃብ አደጋ በዓለማችን በእ.ኤ.አቆጣጠር በ1930ዎቹ ከታየው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አመሳስሎታል ዘገባው የኢትዮጵያው ሁኔታ ከያኔው ሲተያይ ማብቂያ ያለው አይመስልም፡፡
የትግራይ መንግስት ፕሬዚዳንት ትናንት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በጻፉት ግልፅ ደብዳቤ ዛሬ ኢትዮጵያ ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ መዳረጓንና ይህም ለትውልድ የሚተርፍ ቀውስ ማስከተሉን ማመልከታቸው ይታወሳል፡፡
መብራህቱ ይባልህ