Home ዜና የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር በትግራይ ላይ የጤና ስርዓቱ አገልግሎት መስጠት ወደ...

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር በትግራይ ላይ የጤና ስርዓቱ አገልግሎት መስጠት ወደ የማይችልበት  ቁመና  መድረሱን አስታወቁ፡፡

1182

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ከ18 ወራት በላይ በትግራይ ህዝብ  ላይ የቀጠለው ከበባና ክልከላ  ተከትሎ ያጋጠመው የመድሃኒት አቅርቦት እጥረት  አጠቃላይ የጤና ስርዓቱ አገልግሎት መስጠት ወደ የማይችልበት  ቁመና  መድረሱን አስታወቁ፡፡

መቐለ ውስጥ የሚገኝና ለትግራይ ህዝብ ብቸኛ ሪፈራል ሆስፒታል የሆነው የዓይደር  ሆስፒታል ጀነሬቶሮች እና አምቡላንሶች በነዳጅ እጥረት አገልግሎት  መስጠት እያቆሙ ነው፤ ባለሞያዎችም የምግብ እጦት ባስከተለው  ረሃብ ምክንያት ህይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ ወድቋል ብለዋል፡

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም ፋሽስቶችና አምባገነኖች በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖሩት ክልከላ ከ6 ሚሊዮን በላይ የሚሆነውን የትግራይ ህዝብ አሁንም ከበባ ውስጥ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ፋሽስት የአብይ ቡድንና አምባገነኑ ኢሳያስ በትግራይ ህዝብ ላይ ባኖሩት ከበባና ክልከላ የምግብ አቅርቦት ብቻ ሳይሆን እጥረት ያጋጠመው   የነዳጅና የመድሀኒት እቅርቦት ጭምር ነው ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ በዚህ ምክንያትም የትግራይ የጤና ስርአት ኩፍኛ መጎዳቱን ተናግረዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የተሻለውን ለማድረግ ጥረት ያደርጋል ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ ብቸኛው መፍትሄ ግን ፀረ ሰብአዊነት የሆኑ ስራዎችን በማቆም  ዩኩሬን ላይ እንደተፈጠረው ሰላማዊ ሁኔታን መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

የዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆሰፒታል በፋሽሽቱ ቡድን በተደረገው ከበባና ክልከላ ተከትሎ ባጋጠመው የመድሃኒት ኣቅርቦት እጥረት ምክንያት ከሁለት ቀናት በፊት ስራውን ሙሉ በሙሉ  ማቋረጡን  የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረስላሰ መግለፃቸውን ይታወሳል፡፡

የሆስፒታሉ አገልግሎት ማቆም በተለይ ኣዲስ ለሚወለዱ ህፃናትና ቀዶ ጥገና ለሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች ላይ ጉዳቱ የከፋ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

የዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆሰፒታል በመቐለ ዩኒቨርስቲ ስር ሁኖ የሕክምና ትምህርት ከመስጠት በተጨማሪ ከትግራይ፣ ከኣፋር እና ኣጎራባች ክልሎች የሚመጡ ታማሚዎችን የህክምና ኣገልግሎት ሲሰጥ የነበረ መሆኑን ይታወቃል፡፡

በመብራህቱ ይባልህ