Home ዜና የዓዲ ሽሁ ሆስፒታል ሀኪሞች ርሃብ

የዓዲ ሽሁ ሆስፒታል ሀኪሞች ርሃብ

በትግራይ ደቡባዊ ዞን እምባ አላጀ ወረዳ የምትገኘው የዓዲሽሁ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ሰራተኞች ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል፡፡ የእናቶችና ህፃናት ክትትል አስተባባሪ አቶ አባዲ ንጉስና ሲስተር ተክኤን ብርሀኑ በመድሃኒት እጥረት ምክንያት በሆስፒታሉ የሚወልዱ እናቶች ከሃኪሞች አቅማ በላይና የተሟላ አገልግሎት ስለሌለ በቤታቸው የሚሞቱ እናቶችና ህፃናት እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ጎይቶኦም ግርማይ እንዳሉት በመድሃኒት እጦት ምክንያት የተገልጋዮች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መቀነሱን ተናግረዋል፡፡ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ጎይቶኦም ግርማይ እና ዶክተር ገብረ ኪሮስ ተስፋይ የዓዲ ሽሁ እና አከባቢው ታካሚዎች የታዘዘላቸውን መድሃኒት ማግኘት ባለመቻላቸው በባለሞያዎች ፊት ህይወታቸው ሲያልፍ ማየት የተለመደ ተግባር ሆኗል በተለይ ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ያላቸው ወገኖች በብዛት በሞት እያጣናቸው ነው ብለዋል፡፡ የሆስፒታሉ ባለሞያዎች ከ አስር ወር በላይ ያለ ደሞዝ እያገለገሉ የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ግን ራሳቸውና ቤተሰቦቻቸው ለከባድ የርሃብ አደጋ እንዳደተጋለጡ ገልፀዋል፡፡ የጤና ባለሞያዎቹ በከበባና ክልከላው ምክንያት በርሃብ እና በተለያዩ በሽታዎች እየተሰቀየ ያለውን የትግራይ ህዝብ ለማገልገል ቀን እና ሌሊት ባለመታከት በመስራት ላይ እንደሚገኙ ቢገልፁም ከአስር ወራት በላይ ያለ ምንም ደሞዝ መስራት ህይወታቸው ከባድ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡ ሄለን ሀብቱ

1161